ክረምት ከሌለ ሁሉ ቤት…..

ክረምት ከሌለ ሁሉ ቤት….. ክረምትን ከረመ ይለዋል ሥርወ ግሱ፡፡ አንዴ የሚወጣ የሚደርስ ማለትን ይመስላል፡፡ እርግጥ ነው ሶስቱ አፈ ለምለም የሚባሉት ወራት በዓመት አንዴ ይወጡና ልምላሜን፣ ንጽህናንና ተስፋን አብስረው ይመለሳሉ–በአብሳሪ አበባቸው አደይ ታጅበው፡፡ ክረምት መታደስን የሚጠይቅ ወቅት ነው–ራስን በማዘጋጀት መለወጥን፡፡ በበጋ ወይም በሌላ ወቅት ዝግጅታችን እንቀበለው ካልን የአሻዋ መሠረታችንን ሊጠራርገው፣ ጥንካሬ አልባ ድንኳናችንን ሊቀደውና ሜዳ ልናድር... Continue Reading →

መተዛዘል

( click to read pdf ) ጠቢቡ (ጠቢቡ ስል ከእሱ በፊትም ሆነ ከእርሱ በኋላ እርሱ በዚህ ስም የተጠራበትን ያህል ጥበብና እውቀት ያሟሉ እንደሌሉ ልብ ይሏል-ስሙን ወረሱት'ጂ) ይህ ጠቢብ በምድር ላይ በቆየበት እድሜው እጅግ ብዙ የዓለም ክንውኖችና ድርጊቶችን፣ስሪቶችና ሂደቶች፣ቅዠቶችና ምኞቶች… ወዘተ ሁሉን አሰሰ፤ የምድር ጥበባት፣ፍልስፍናዎች፣ ምስጢራትና ህላዌዋን ሁሉ መረመረ፤አመሠጠረ፡፡ በጥበቡ ቃልም መሐል ይኽን የሚደንቅ ምስጢር አረቀቀ፡፡... Continue Reading →

ያልሞተው ሟች

( click to read pdf) ቅድመ አግድም…… ከቁሙ አፈር ላይ አፈር አልባ ወዙ             ተራ ላብ እንዳይሆን ጨው ጨምሮበት ለቁልሉ አፈር ጣይሙን 'ዲጣፍጥ           ሕይወት 'ዲዘራ ወዙን ቢቀዳለት አፈር ውኃ ወሰደው አፈር አፈር በላው          'ሚሉት ትርጓሜ ዘመኑ አለፈ ሲፈጠር ከአፈር ሲፈርስ ወደአፈር         እርባን የለሽ ትረጉም የቀድሞ ታጠፈ፡፡ አፈር ወዝ... Continue Reading →

እድሜ ዘመን ቁጥር

እድሜ ዘመን ቁጥር ህልውናዬ ጸድቆ እስትንፋስን ስ'ቸር እኩል ዘመን ሰፈርን እድሜዬና ምድር እሷ ……. የዓመት ትግሏን ጨርሳ በወቅት ስትከፈል ከጽጌ 'ቅፍ ገብታ ድካሟ ተረስቶ መንፈሷ ታድሷል እድፍ ገላዋ ነጽቶ ባ'ዲስ ልብስ ሸብርቋል ይኽን ትቆጥራለች…………. አንድ ሁለት እያለች፡፡ እኔ………. ፍላጎቴ በዝቶ መልኬ ተቀይሯል ሥጋዬ ጀግኖ ዓለሙ ጠቦኛል እኔም እቆጥራለሁ…….. አንድ ሁለት እላለሁ የእድሜዬን ወረት ባዶ እያስቀረሁ፡፡... Continue Reading →

እንደ መግቢያ

አለማወቅ መልካም ፪                                           ከአውቃለሁ እውቀቱ                                                   አለማወቁን ካወቀው                                           ያ………. አ'ለማወቅ መልካም ነው!! የካቲት ፳፻ዓ.ም አዲስ አበባ

Start a Blog at WordPress.com.

Up ↑