አትቀስቅሷቸው!

አትቀስቅሷቸው በሰላም ይረፉ፡ አትቀስቅሷቸው አትዘኑላቸው አታልቅሱላቸው። ራሄልም የለች፡ ዕንባዋ 'ሚሻገር ሙሴን 'ሚጠራ፡ ከጸባዖት ቅጽር ለእኛው እናልቅስ ልጅነት ህሊና፡ ላስጨነገፈ ነፍስ እናትነትን፡ ላዘነፈ ሀዘን እምነትን፡ ለዘረፈ። ለ'ኛ ፈርዖኖች ለልበ ደንዳና ለጭካኔ ጀግና ከጎጥ ሰው ፈንካች ለአዛኝ ቅቤ አንጓች ለሚወድ በጭፍን፡ ሚጠላ በድፍን ለአዞ እ'ባ አፍላቂ፡ መርጦ ለሚያዝን። ይሂዱ ይተኙ፡ እነሱስ አረፉ በእኛው ኃጢያት ለጽድቅ ተሰለፉ ልመናስ... Continue Reading →

በእንተ ጾም

በ pdf ለማንበብ እዚህ ይጫኑ ጾም ከኃጢአት ወይስ ከምግብ መከልከል?የጥሉላት ምግቦች ርኩሳን ናቸውን?ሥጋ በፍላጎቱ ላይ ልጓም ያስፈልገዋልን?ሁሉን እንበላ ዘንድ አልተፈቀደምን?የጾም በያይነቱ- እንደመካሻ?መጠጥ፣ ሩካቤ ሥጋና ጾምጋድ፣ ቅዳሴና በዓል በነብያት ጾም እንደ መግቢያ . . .. የሰዎች የአኗኗር ዘይቤ መቀየር፣ የባህል፣ ልማድና ትውፊት መወራረስ፣ የቄሳር ዐለም ርዕዮት መለዋወጥና የመሳሰሉት ጉዳዮች የአስተሳሰባችንን አቅጣጫ፣ እይታና አረዳድ ይሞርዱታል፣ ያርሙታል። የዚህ... Continue Reading →

መጪው ጊዜ ከዐብይ ጋር!

መንግሥት በሽብርተኝነት ለፈረጃቸው ተቃዋሚ ቡድኖች የሽብርተኝነት ፍረጃውን በማንሳት ትልቅ ርምጃ ወስዷል፡፡ ጸረ-ሽብር ሕግ አንስቶ የምህረት አዋጅ አጽድቋል፡፡ ይህንኑ ርምጃ ተከትሎ በሽብር ተከሰው የነበሩ ፖለቲካ ቡድኖች ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ ጥሪ አድርጓል፡፡ በሌላ በኩል ብሄርተኞች የክልልነት፣ የሙስሊም መብት ተሟጋቾች ደሞ ነባር ጥያቄያቸውን እያሰሙ ያሉት ለውጡን ለመጠቀም ነው፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደሞ በውጭ ሀገራት ያሉ የተቃራኒ ፖለቲካ ቡድኖች ጠቅላይ ሚንስትሩ ያቀረቡትን ጥሪ ተቀብለው ወደ ሀገር መግባታቸውን በበጎ የሚያዩት እንዳሉ ሁሉ በስጋት የሚያዩትም ወገኖች አልጠፉም፡፡ እናም ቡድኖቹ ተቃራኒ ፍላጎቶቻቸውን እና ፖለቲካዊ አጀንዳዎቻቸውን በምን መልኩ ያንጸባርቁ ይሆን? ቡድኖቹ ባንድ ጊዜ መሰባሰባቸው ለሀገሪቷ ምን ዐይነት ትሩፋት እና ስጋት ይፈጥር ይሆን? ሁኔታው በጠቅላላው ምን ዐይነት ቅራኔዎችን እና ግጭቶችን ሊፈጠር ይችላል?

ዶ/ር አብይ አህመድ ከኃይለማርያም ደሳለኝ በምን ይለያሉ?

በተለይ ዶክተር አብይ እንደ አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሁሉ የግንባሩ አስኳል ከሆነው ሕወሃት ውጭ የተመረጡት ስለሆኑ ለሩብ ክፍለ ዘመን ጭቆና የመረረውን ሕዝብ ወደ ቃል ኪዳኗ ምድር የሚያደርሱ ሐዋሪያ አድርጎ ማየት በምንም መልኩ የሚያዋጣ አይደለም፡፡

ኦቦ ለማና ህወሃት

አቶ ለማ መገርሳ የመንግስት ባለስልጣን ሆኖ በቆየበት ጊዜ ሁሉ ሲያስገድል፣ በሀሰት ሲያስወነጅል፣ ሕዝብን ከሕዝብ ሲያባላ እና በድህነት እንድንሰቃይ ለሙስና ሲያጋፍር ነው የኖረው። ሌላውን የኢህአዴግ ባለስልጣን አስኮንኖ፣ አቶ ለማ እና ዶ/ር ዐብይን ነጻ የሚያስወጣ ምንም ዓይነት ምክንያት የለንም። ማሽሞንሞን ሳያስፈልግ፥ አቶ ለማ መገርሳ የኢህአዴግ ሽንት ጨርቅ ነው። የአምባገነን ስርዓት ሽንት እንዳይታይ በማድረግ ረገድ የሚጫወተው የዳይፐርነት ሚና... Continue Reading →

ከደርግ ወደ ጎሣዊ ደርግ- “ግንቦት 20” (ክፍል ፮)

የአንድ ጎጥ የበላይነትና የመበታተን አደጋ! ራሳቸውን “የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር” ብሎ በመሰየም የትግራይን ሕዝብ ሽፋን በማድረግ፤ “የምታገለው ለአንተ ነጻነት ነው” በማለት፤ መልሶ እታገልለታለሁ ያለውን ሕዝብ ያስጨፈጨፈው፣ ያስራበው፣ የግፈ ሰለባ ያስደረገው፣ … ራሱን ህወሓት እያለ የሚጠራው የወንበዴዎች ቡድን የኢትዮጵያን የሥልጣን መንበር ከተቆናጠጠ በኋላ የትግራይ ሰዎችን በሌላው ኢትዮጵያዊ ለማስጠላትና “ስም ለማሰጠት” እንዲሁም ለማጠልሸት ባለፉት 26ዓመታት ሲሰራ... Continue Reading →

ከደርግ ወደ ጎሣዊ ደርግ- “ግንቦት 20” (ክፍል ፭)

ኢትዮጵያዊነትና ሰላማዊው ትግል መርዛማ ፍሬ 7፡  የኢትዮጵያዊነት ፈተና! ባሳለፍነው ሩብ ክፍለ ዘመን ከአካባቢያዊ ማንነትና ከጎሣ በተሻገረ ለኢትዮጵያዊነት መታመን ህይወትን እስከማጣት የሚደርስ ዋጋ የሚያስከፍል አደጋ ሆኗል። እስር፣ እንግልት፣ ስቅየት፣ ስደት፣ እልፍ ሲል ደግሞ ሞት በኢትዮጵያዊነት የመታመን አደጋዎች ናቸው። በዜግነት ማዕቀፍ የሚተረጎም የጋራ ማንነት በቀጨጨባት ኢትዮጵያ ዘውጋዊ ማንነት የፖለቲካ ሜዳው መገለጫ ሆኗል። ዘመናዊት ኢትዮጵያ እንደ አገር እውን... Continue Reading →

ከደርግ ወደ ጎሣዊ ደርግ- “ግንቦት 20” (ክፍል ፬)

የመንግስት ውሸትና የሃይማኖት ተቋማት ውድቀት የትግራይ ሕዝብ “ነጻ አውጡኝ” ብሎ ሳይሰይማቸው፣ ሳይመርጣቸው፣ ሳይጠይቃቸው፣ ራሳቸውን “የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር” ብለው የሰየሙ ወንበዴዎችና ሽፍቶች የምኒልክ ቤተመንግሥት ከገቡ 26 ዓመታት ተቆጥረዋል። በቂም፣ በበቀል፣ በክፋትና በኢሞራላዊ ተግባራት የተሞሉ፤ ኢትዮጵያዊ መሆናቸው ፈጽሞ የሚያጠራጥር፤ ማንነታቸው ይህ ነው ተብሎ የማይታወቅ፤ በሐሰት ስም ከበረሃ እስከ ቤተመንግሥትና ዓለምአቀፍ መድረክ ላይ የታዩ፤ በሐሰት ፕሮፓጋንዳ... Continue Reading →

ከደርግ ወደ ጎሣዊ ደርግ- “ግንቦት 20” (ክፍል ፫)

ስደት በመጀመሪያው ከደርግ ወደ ጎሣዊ ደርግ- “ግንቦት 20” (ክፍል ፩) ጽሑፍ ከ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች መሃል ስለከሸፈው የፌዴራል ሥርዓት እና የትምህርት ፖሊሲው ክስረት ማተታችን ይታወሳል። በሁለተኛው ክፍል ሰለ መሬት ነጠቃ አስነብበናል በዚህኛው ክፍል ሁለት ደግሞ የአፓርታይዳዊ አገዛዝ አራማጁ ህወሓት ሥልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ከዘራቸው በርካታ መርዛማ ፍሬዎች መካከል ቀጣዩን ከማሳያዎች ጋር ማስነበባችን እንቀጥላለን። መርዛማ ፍሬ 4፡ ስደት የኢትዮጵያዊያን... Continue Reading →

ከደርግ ወደ ጎሣዊ ደርግ- “ግንቦት 20” (ክፍል ፪)

የመሬት ነጠቃ በረዥሙ የኢትዮጵያ ታሪክ በአስተዳደሩ ተመስግኖ በክብር የተሸኘ ገዥ ስለመኖሩ የሚያወሳ ታሪከ-ድርሳን ፈልጎ ማግኘት የሚቻል አይመስልም። ሁሉም አገዛዞች የተወገዱት በአመፅ አልያም በተፈጥሮ ሞት ነው። ልክ የዛሬ 26 ዓመት 1983 ዓ.ም. ወርሃ ግንቦት በምዕራቡ አለም ረዳትነት በጠመንጃ ወደ ሥልጣን የመጣው አፓርታይዳዊው የህወሓት ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ በቀደሙት ገዥዎች የብረት ጫማ ውስጥ ተከልሎ አፈናና ግድያውን “ግፋ በለው!”... Continue Reading →

Start a Blog at WordPress.com.

Up ↑