አትቀስቅሷቸው!

አትቀስቅሷቸው በሰላም ይረፉ፡ አትቀስቅሷቸው አትዘኑላቸው አታልቅሱላቸው። ራሄልም የለች፡ ዕንባዋ 'ሚሻገር ሙሴን 'ሚጠራ፡ ከጸባዖት ቅጽር ለእኛው እናልቅስ ልጅነት ህሊና፡ ላስጨነገፈ ነፍስ እናትነትን፡ ላዘነፈ ሀዘን እምነትን፡ ለዘረፈ። ለ'ኛ ፈርዖኖች ለልበ ደንዳና ለጭካኔ ጀግና ከጎጥ ሰው ፈንካች ለአዛኝ ቅቤ አንጓች ለሚወድ በጭፍን፡ ሚጠላ በድፍን ለአዞ እ'ባ አፍላቂ፡ መርጦ ለሚያዝን። ይሂዱ ይተኙ፡ እነሱስ አረፉ በእኛው ኃጢያት ለጽድቅ ተሰለፉ ልመናስ... Continue Reading →

ኦሮማይ-በበአሉ ግርማ

በበአሉ ግርማ ከጎራው ዘልቄ እስኪ ልነጋገር ካለሰው ቢወዱት ምንያደርጋል ሃገር? የኔ ውብ ከተማ ህንጻ መች ሆነና የድንጋይ ክምር የኔ ውብ ከተማ መንገድ መች ሆነና የድንጋይ አጥር የኔ ውብ ከተማ የኔ ውብ አገር የሰው ልጅ ልብ ነው የሌለው ዳርቻ የሌለው ድንበር፡፡ ህንጻው ምን ቢረዝም ምን ቢጸዳ ቤቱ መንገዱ ቢሰፋ ቢንጣለል አስፋልቱ ሰው በሰው ካልሸተተ ምንድነው ውበቱ?... Continue Reading →

እኛ

https://soundcloud.com/atuadub/enya    ላይ የተደመጠ በትግስት ማሞ እኛ ን'ጎርሰው ሳይኖረን እኖረው ሳይኖረን ባዶ ተስፋ መሐል መጪውን ሞሽረን የሰጡንን ቀምሰን ባሉን አሜን ብለን ባንድዬ ቸርነት አይችሉትን ችለን ተገፍቶ የማያልቅ ጉድ ዘመን ተሻግረን ይኸው ዛሬም አለን ህልማችን መሐል ላይ ስደት ተስሎበት በልባችን ሙሉ ራስ መውደድ በቅሎበት ኑሯችን ጫፉ ላይ ፍርሃት ቋጥረንበት እምኝ ብርቃችን ነው መዘመን ከሆነ አዎን ዘምነናል... Continue Reading →

ናፍቆቴ ነበርሽ…

ግጥሙን ለማድመጥ እዚህ ይጫኑ  ናፍቆቴ ነበርሽ… የዘመን ድልድዬ … ተስፋ እየመገብሽኝ ጣዕምሽ አልባሴ ….. ፍቅርሽ ኑሮ ሆነኝ፡፡ በኑሮሽ ታዛ ስኖር ተጠግቼ ረሃብ ጠግቤ በጥማት ረክቼ እያለምኩሽ ነበር ገላሽን ጓጓቼ፡፡ እድሜን የሚያረዝመው የገላሽ ውበቱ ክንድን የሚያፋፋው የሚፋጅ ሙቀቱ ንጉስ ከናሽከሩ እተቧጠረ ይታደስበታል ክብርሽ በየአልጋው እየተደፈረ ተጋልጦ ይታያል ያቀፈም የተኛም ለገላሽ ዘብ ሁኖ ይዋደቅለታል፡፡ አይኔ እስኪጨልም፣ የምኞት... Continue Reading →

የዘመን ኅዳግ

  Toread in pdf click የዘመን ኅዳግ    መታሰቢያይሁን ዘመን ለጠፋው ዘመን ከኮሮጆው ከማደሪያው ገባ እጥፋት አበጀ ምዕቱን ከምዕት ሺህውን በሺህ አጥፍቶ ጥንተቱን አወጀ ከዘመኑ ድንበር ከማማው ላይ ቆሞ                      ልባሙ፡ ሕይወት እየሳለ ምልሰቱን ጀመረ “ዘመኑ ገር ሞልቶት ጥጋብ ትርጉም አ'ቶ ሰልጥኖ ነበረ ብዙዎች ተኝተው ሲያንኮራፉ ሳለ ከዚ'ች ሃገር ላይ እንቅልፍ ተሰደደ ሁሉም እየተጋ በእውቀት ሲታነጽ... Continue Reading →

ምንድነው ደስታ ?

ምንድነው ደስታ ምንድነው እርካታ ገላን ለረፍት ሰ’ቶ ህሊናን ‘ሚረታ ሠላም ዙሪያን ከቦ መንፈስ ‘ሚገዛ! ጥያቄስ ምንድነው ምንድምን ፍለጋ እድሜ ዘመን ሙሉ ላይመጣ ጥበቃ! መኖር ነው ደስታ ደስታን መሻት እርካታ ‘ምንድር’ ነው ትርጉሙ ሚታሰር ሲፈታ። ሰኔ 2004

መድኃኒት

ሆሣዕና በአርያም!  ሆ..ሣ.ዕና በአ…ር.ያም! በአርያም በልዕልና ጸንቶ የሚኖር ከአርያም የተገኘ መድኃኒት ማለት ነው። እምሆሣዕናሁ (መድኃኒት ከመሆኑ የተነሣ) አርአየ ተአምረ ወመንክረ-- ፍጹም ተአምራቱን ገለጸ አእምሮ ጠባይ ያልቀናላቸውን ሕፃናት አእምሮ ጠባይ ቀንቶላቸው፤ ንባበ አእምሮ ለሌላቸው አዕባን ንባብ አእምሮ ሰጥቶ እንዲያመሰግኑት አድርጓል። ግትነቱን ገልጦ።  አርአየ ጸጋ ወኃይለ-- ከሥልጣኑ ሳይለይ በጽርሐ አርያም በዘባነ ኪሩብ ባለ በምድር ልጅነትን ከሃሊነትን ገለጸ።... Continue Reading →

ሴንሰርሺፕ!

በነብይ መኮንን ሴንሰርሺፕ! አይጢቷ ግጥም ፃፈች፣ ርዕሱ “ድመት” የሚል “ድመት ባይርባት ኖሮ፣ አታሳድደኝም ነበር” ብላ ብዕሯን በመቀመር፡፡ ድመት ያንን አገኘች፤ “አይጥ” የሚል ርዕሱ፤ የመልስ - ምት ግጥም ፃፈች “ከአፈጣጠሯ ነው እንጂ! ድመት ጨካኝ እንዳልሆነች፡፡” የቤቱ ባለቤት ሰውየ ፣ የሁለቱን ግጥም አገኘ፣ “አሃ! ተነሱብኝ ማለት ነው!? አደጉና በኔ ላይ፣ ግጥም መፃፍ ጀመሩ? እንደተኛሁ በጭለማ፣ ነቅተው ወረቀት... Continue Reading →

1..2..3..

ትላንት…. ነብያት ተመኙ ከምላሳቸው ቃል ምድር ላይ 'ዲያዩ መባዘኑ ቀርቶ ባርነት አብቅቶ ተስፋ 'ዲገበዩ ግና.. ስቃያቸው በዝቶ ጽድቃቸው ዋጋ'ቶ የመርገም ጨርቅ ሆነ ኃጢአትን ተዋልደው በውርስ ተቀባብለው ነፍሳቸው ጣመነ፡፡ ያኔ.. እንባን ማበሻ የተስፋ ቀን ሲደርስ አርያም ተከፈተ በበረትም ሲገኝ ነጻነት አውጆ ሰላምን አተተ ምድር በይቅርታ በም'ረት ተከድና ፍቅር በረከተ ዛሬ…. እኒያ ደስታዎች ለታሪክ ተትተው ዘመናት አለፉ... Continue Reading →

ፈኑ እዴከ

ሠላም! እንዴት ሰነበታችሁልኝ መቼም ምስጋናዬ እጅጉን የበዛ ነው፡፡ የጦማሬ ተከታታይ ናችሁና፡፡ በምታገኟቻ ጦማሮች ላይ ያላችሁንና የተሰማችሁን ብትጽፉልኝ ደስታዬ ወደር አልባ ይሆናል፡፡ ትንሽ ጠፍቻለሁና ከይቅርታ ጋር እንኳን ለበዓለ ልደት መዳረሻ አደረሳችሁ በማለት ይቺን ጀባ ብያለሁ፡፡ ፈኑ እዴከ “በ የትውልዳችን በዘመናት ሐረግ በዛ ልመናችን ተስፋችን ቃልኪዳኑ ርቆ ባርነት ተሰጠን ጽድቃችን ድካሙ ዋጋ'ቶ የመርገም ጨርቅ ሆነ ኃጢአትን በውርስ... Continue Reading →

Start a Blog at WordPress.com.

Up ↑