To Read in PDF ሲዳሩ ማልቀስ-አግብቶም ማልቀስ እንኳን ለወርኃ ሚያዝያ- ወርኃ መራዊ አደረሳችሁ አደረሰን። መቼም ጊዜው የሰርግም አይደል ዘንድሮ ሚያዝያ ቢወጣብንም ቅሉ። የፈጣሪያቸው ሙሽራ ይሆኑ ዘንድ ራሳቸውን ለጃንደረባነት የለዩ ብዙዎችን አይተናል። እንደኔ አይነቱ ደግሞ “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ..” የሚለውን እያሰበ ብቻነቱን ሊረሳ ይሞሸራል፤ያገባል። ሁለቱም የተገባ ሕይወት ነውና እግዚአብሔር የልባቸውን መሻት ይሙላላቸው። ደስታን ይዛቁ-እርካታን ይሞሉ። ጋብቻ... Continue Reading →
የሕማም ሰው
To read in PDF please click የሕማም ሰው “መልክና ውበት የለውም፣ ባየነው ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም። የተናቀ ከሰውም የተጠላ፣ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፤ እኛም አላከበርነውም” ኢሳ 53፡2-3 “የሚሠዋ በግ እርሱ ነው፤ የሚሠዋ ካህን እርሱ ነው። ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም መሥዋዕት የሚቀበል እርሱ ነው።... Continue Reading →
መድኃኒት
ሆሣዕና በአርያም! ሆ..ሣ.ዕና በአ…ር.ያም! በአርያም በልዕልና ጸንቶ የሚኖር ከአርያም የተገኘ መድኃኒት ማለት ነው። እምሆሣዕናሁ (መድኃኒት ከመሆኑ የተነሣ) አርአየ ተአምረ ወመንክረ-- ፍጹም ተአምራቱን ገለጸ አእምሮ ጠባይ ያልቀናላቸውን ሕፃናት አእምሮ ጠባይ ቀንቶላቸው፤ ንባበ አእምሮ ለሌላቸው አዕባን ንባብ አእምሮ ሰጥቶ እንዲያመሰግኑት አድርጓል። ግትነቱን ገልጦ። አርአየ ጸጋ ወኃይለ-- ከሥልጣኑ ሳይለይ በጽርሐ አርያም በዘባነ ኪሩብ ባለ በምድር ልጅነትን ከሃሊነትን ገለጸ።... Continue Reading →
ተ….መጽዋቹ
ተ….መጽዋቹ በየቤተ ክርስቲያኑ አጥር፣ በየመኪና መንገዱና በየመጓጓዣ ሥፍራ የልመና መስፋፋት ምን የሚያስከትል ይመስልዎታል? ለጋሽ በበዛበት ከተማ ለማኝ ቢበዛስ ምኑን ይገርማል? ለመሆኑ እርስዎ በቀን/በሣምንት ምን ያህል ለኔ ቢጤ (ለነዳይ) ይሰጣሉ? በወር ምን ያህል ወጪ ይሆንልዎታል ማለት ነው? ‘ቀኝህ ስትሰጥ ግራህ እንዳታይህ’ ስለተባለ አላውቀውም ቢሉን ጉዳያችን አልጣመዎትም ማለትን ይመስላል። መስጠቱም መድረሱም መልካም ፤ጥያቄው ግን ምን ያህል መፍትሄ... Continue Reading →
ምንትኑ ጌጋየ ለዝ ብእሲ
To read in pdf click ምንትኑ ጌጋየ ለዝ ብእሲ የጲላጦስ ነገር የሚደንቅ ነው! የዘመኑ ድንቅ አሳቢ ነበርና፡፡ ዓለም ሁሉ የሚጠይቀውን እርሱ ደፍሮ ጀምሮት ተመዝግቧል–እውነት ምንድነው? ብሎትም የለ፡፡ የረቀቀና እጅግ ከማሰብ የሚመነጭ ጥያቄ ነው፡፡ ከስሜት ህዋሱ መረዳት በላይ የሆነበት፡፡ ታዲያ ግን ይህን አሳቢ ምንም ሳይቆይ እንዲህ ሲል የሰማነው ለምንድነው? “የዚህ ሰው ስህተቱ ምንድን ነው? ምትኑ ጌጋየ... Continue Reading →
ሴንሰርሺፕ!
በነብይ መኮንን ሴንሰርሺፕ! አይጢቷ ግጥም ፃፈች፣ ርዕሱ “ድመት” የሚል “ድመት ባይርባት ኖሮ፣ አታሳድደኝም ነበር” ብላ ብዕሯን በመቀመር፡፡ ድመት ያንን አገኘች፤ “አይጥ” የሚል ርዕሱ፤ የመልስ - ምት ግጥም ፃፈች “ከአፈጣጠሯ ነው እንጂ! ድመት ጨካኝ እንዳልሆነች፡፡” የቤቱ ባለቤት ሰውየ ፣ የሁለቱን ግጥም አገኘ፣ “አሃ! ተነሱብኝ ማለት ነው!? አደጉና በኔ ላይ፣ ግጥም መፃፍ ጀመሩ? እንደተኛሁ በጭለማ፣ ነቅተው ወረቀት... Continue Reading →
ምን ዓይነት ለውጥ?
ምን ዓይነት ለውጥ? የብዙህ ሰው ሐሳብ ይመስለኛል-በውስጣችን የነበረው። ባ’ንድ ወቅት ካ’ንድ ወንድሜ ጋር ኢትዮጵያ አሁን ስላላት መልክ (ምን እንደምትመስል) ለመሳል ስንሞክር ነበር- በመስመር ሳይሆን በቃላት ጨዋታ። እርግጥ ቀላል ነው ማንኛውም ሰው ኢትዮጵያ እንዴት ሆና ልታያት ትፈልጋለህ ተብሎ ቢጠየቅ “በቴክኖሎጂና ፈጠራ የበለጸገች” “ከድህነት የተላቀቀች” “ዲሞክራሳዊ አስተዳደርና ሥርዓት የተሟሉላት..” የመሳሰሉትን መመለሱ አይቀርም። እኛም በጥቅሉ እንዲሁ ብለን ነበር።... Continue Reading →
‘የጥራት አምባሳደሮች’ ዩኒቨርስቲ ኮሌጆቻችን
‘የጥራት አምባሳደሮች’ ዩኒቨርስቲ ኮሌጆቻችን click to Read in pdf ‘የጥራት አምባሳደር’ የሚለው ሐረግ ምናልባት የቅ/ጊዮርጊስ ቢራ ማስታወቂያን ያስታውሰን ይሆናል። ጥራት የሚለው ጽንሰ ሐሳብ ሁሌም አሻሚና አነጋጋሪ ቢሆንም እንደየሙያው አግባብ ትርጓሜ ተሰጥቶት ፤ቢተገበርም ባይተገበርም ጥቅም ላይ ውሎ ይገኛል። አልኮልና ለስላሳ ድብልቅ ምሩቃን እያመረቱ የሚገኙት የትምህርት ፋብሪካዎቻችንም መፈክራቸው ይሔው ሀረግ ነው። ‘የልቀት ት/ት ቤት’ ‘ጥራት ላለው ት/ት... Continue Reading →
የኢትዮጵያዊት ቤተ ክርስቲያን የፓትሪያርክ ምርጫ ውጤት
የኢትዮጵያዊት ቤተ ክርስቲያን የፓትሪያርክ ምርጫ ውጤት በጊዜ መሬቱን ያዘጋጀ ፍሬውን ዘራ በወቅቱ ፍሬውን የዘራም ከጎተራው አከማቸ! "ነጻ ፍትሃዊና ተአማኒ ምርጫ ነበር! ብሎ ነበር "መለስ
ትልቅ መጥበሻ
ትልቅ መጥበሻ ቆም ብለን ሰዎችን ብንመለከት እያንዳንዱ ሰው የሆነ አንድ ቦታ ተጣብቆ ያለ ነው የሚመስለው፡፡ በሕይወታቸውም ውስጥ አንዳንዴ እንዲሁ ነው፡፡ አንዳንዶች በየቤቶቻቸው ሥራዎች ተጠምደው የተጣበቁ ሲሆን፤ ከከበባቸው ሁናቴ ጋር የተጣበቁ ወይም ይቀየራል፣ ይሻሻላል፣ ወይም ይለወጣል ብለው ተስፋ ባላደረጉት ሥራ ላይ ሙጥኝ ብለው ተጣብቀው ይኖራሉ። ሌሎችም ከልምዶቻቸው ጋር ደንዝዘው በሕይወታቸው ብርሃን አልባ ድንግዝግዝ ውስጥ ተጣብቀው ይገኛሉ።... Continue Reading →