አትቀስቅሷቸው በሰላም ይረፉ፡ አትቀስቅሷቸው አትዘኑላቸው አታልቅሱላቸው። ራሄልም የለች፡ ዕንባዋ 'ሚሻገር ሙሴን 'ሚጠራ፡ ከጸባዖት ቅጽር ለእኛው እናልቅስ ልጅነት ህሊና፡ ላስጨነገፈ ነፍስ እናትነትን፡ ላዘነፈ ሀዘን እምነትን፡ ለዘረፈ። ለ'ኛ ፈርዖኖች ለልበ ደንዳና ለጭካኔ ጀግና ከጎጥ ሰው ፈንካች ለአዛኝ ቅቤ አንጓች ለሚወድ በጭፍን፡ ሚጠላ በድፍን ለአዞ እ'ባ አፍላቂ፡ መርጦ ለሚያዝን። ይሂዱ ይተኙ፡ እነሱስ አረፉ በእኛው ኃጢያት ለጽድቅ ተሰለፉ ልመናስ... Continue Reading →