መጪው ጊዜ ከዐብይ ጋር!

መንግሥት በሽብርተኝነት ለፈረጃቸው ተቃዋሚ ቡድኖች የሽብርተኝነት ፍረጃውን በማንሳት ትልቅ ርምጃ ወስዷል፡፡ ጸረ-ሽብር ሕግ አንስቶ የምህረት አዋጅ አጽድቋል፡፡ ይህንኑ ርምጃ ተከትሎ በሽብር ተከሰው የነበሩ ፖለቲካ ቡድኖች ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ ጥሪ አድርጓል፡፡ በሌላ በኩል ብሄርተኞች የክልልነት፣ የሙስሊም መብት ተሟጋቾች ደሞ ነባር ጥያቄያቸውን እያሰሙ ያሉት ለውጡን ለመጠቀም ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደሞ በውጭ ሀገራት ያሉ የተቃራኒ ፖለቲካ ቡድኖች ጠቅላይ ሚንስትሩ ያቀረቡትን ጥሪ ተቀብለው ወደ ሀገር መግባታቸውን በበጎ የሚያዩት እንዳሉ ሁሉ በስጋት የሚያዩትም ወገኖች አልጠፉም፡፡ እናም ቡድኖቹ ተቃራኒ ፍላጎቶቻቸውን እና ፖለቲካዊ አጀንዳዎቻቸውን በምን መልኩ ያንጸባርቁ ይሆን? ቡድኖቹ ባንድ ጊዜ መሰባሰባቸው ለሀገሪቷ ምን ዐይነት ትሩፋት እና ስጋት ይፈጥር ይሆን? ሁኔታው በጠቅላላው ምን ዐይነት ቅራኔዎችን እና ግጭቶችን ሊፈጠር ይችላል?

ዶ/ር አብይ አህመድ ከኃይለማርያም ደሳለኝ በምን ይለያሉ?

በተለይ ዶክተር አብይ እንደ አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሁሉ የግንባሩ አስኳል ከሆነው ሕወሃት ውጭ የተመረጡት ስለሆኑ ለሩብ ክፍለ ዘመን ጭቆና የመረረውን ሕዝብ ወደ ቃል ኪዳኗ ምድር የሚያደርሱ ሐዋሪያ አድርጎ ማየት በምንም መልኩ የሚያዋጣ አይደለም፡፡

Start a Blog at WordPress.com.

Up ↑