ምንድነው ደስታ ?

ምንድነው ደስታ ምንድነው እርካታ ገላን ለረፍት ሰ’ቶ ህሊናን ‘ሚረታ ሠላም ዙሪያን ከቦ መንፈስ ‘ሚገዛ! ጥያቄስ ምንድነው ምንድምን ፍለጋ እድሜ ዘመን ሙሉ ላይመጣ ጥበቃ! መኖር ነው ደስታ ደስታን መሻት እርካታ ‘ምንድር’ ነው ትርጉሙ ሚታሰር ሲፈታ። ሰኔ 2004

ምንትኑ ጌጋየ ለዝ ብእሲ

To read in pdf click ምንትኑ ጌጋየ ለዝ ብእሲ የጲላጦስ ነገር የሚደንቅ ነው! የዘመኑ ድንቅ አሳቢ ነበርና፡፡ ዓለም ሁሉ የሚጠይቀውን እርሱ ደፍሮ ጀምሮት ተመዝግቧል–እውነት ምንድነው? ብሎትም የለ፡፡ የረቀቀና እጅግ ከማሰብ የሚመነጭ ጥያቄ ነው፡፡ ከስሜት ህዋሱ መረዳት በላይ የሆነበት፡፡ ታዲያ ግን ይህን አሳቢ ምንም ሳይቆይ እንዲህ ሲል የሰማነው ለምንድነው? “የዚህ ሰው ስህተቱ ምንድን ነው? ምትኑ ጌጋየ... Continue Reading →

1..2..3..

ትላንት…. ነብያት ተመኙ ከምላሳቸው ቃል ምድር ላይ 'ዲያዩ መባዘኑ ቀርቶ ባርነት አብቅቶ ተስፋ 'ዲገበዩ ግና.. ስቃያቸው በዝቶ ጽድቃቸው ዋጋ'ቶ የመርገም ጨርቅ ሆነ ኃጢአትን ተዋልደው በውርስ ተቀባብለው ነፍሳቸው ጣመነ፡፡ ያኔ.. እንባን ማበሻ የተስፋ ቀን ሲደርስ አርያም ተከፈተ በበረትም ሲገኝ ነጻነት አውጆ ሰላምን አተተ ምድር በይቅርታ በም'ረት ተከድና ፍቅር በረከተ ዛሬ…. እኒያ ደስታዎች ለታሪክ ተትተው ዘመናት አለፉ... Continue Reading →

ምድርን የመረገጥ እምነት

ምድርን የመረገጥ እምነት Click to read in pdf ህጻኑ ከተወለደ ፮ ወር ቢሆነው ነው፡፡ ከመዳሁ ለመገላገል አንድ የዘየደውን መላ በመለማመድ ላይ ይገኛል፡፡ የአልጋ፣ የወንበር.. ሌላም ቁስ በመያዝ የመቆምና ለመሄድ የመውተርተር ፍላጎት አዕምሮውን ሞልቶታል፡፡ ስለዚህም ይጥራል አሁንም ይጥራል፡፡ በዚህ ሙከራ ውስጥ የተረዳው አንዳች እውቀት ቢኖር ጠንካራ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ነው፡፡ ምርኩዝ የሚሆነው የማይታጠፍ እጅ ወይም እቃ ካገኘ... Continue Reading →

Start a Blog at WordPress.com.

Up ↑