ከ https://soundcloud.com/atuadub/enya ላይ የተደመጠ በትግስት ማሞ እኛ ን'ጎርሰው ሳይኖረን እኖረው ሳይኖረን ባዶ ተስፋ መሐል መጪውን ሞሽረን የሰጡንን ቀምሰን ባሉን አሜን ብለን ባንድዬ ቸርነት አይችሉትን ችለን ተገፍቶ የማያልቅ ጉድ ዘመን ተሻግረን ይኸው ዛሬም አለን ህልማችን መሐል ላይ ስደት ተስሎበት በልባችን ሙሉ ራስ መውደድ በቅሎበት ኑሯችን ጫፉ ላይ ፍርሃት ቋጥረንበት እምኝ ብርቃችን ነው መዘመን ከሆነ አዎን ዘምነናል... Continue Reading →