የሕማም ሰው

To read in PDF please click የሕማም ሰው “መልክና ውበት የለውም፣ ባየነው ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም። የተናቀ ከሰውም የተጠላ፣ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፤ እኛም አላከበርነውም” ኢሳ 53፡2-3 “የሚሠዋ በግ እርሱ ነው፤ የሚሠዋ ካህን እርሱ ነው። ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም መሥዋዕት የሚቀበል እርሱ ነው።... Continue Reading →

ምንትኑ ጌጋየ ለዝ ብእሲ

To read in pdf click ምንትኑ ጌጋየ ለዝ ብእሲ የጲላጦስ ነገር የሚደንቅ ነው! የዘመኑ ድንቅ አሳቢ ነበርና፡፡ ዓለም ሁሉ የሚጠይቀውን እርሱ ደፍሮ ጀምሮት ተመዝግቧል–እውነት ምንድነው? ብሎትም የለ፡፡ የረቀቀና እጅግ ከማሰብ የሚመነጭ ጥያቄ ነው፡፡ ከስሜት ህዋሱ መረዳት በላይ የሆነበት፡፡ ታዲያ ግን ይህን አሳቢ ምንም ሳይቆይ እንዲህ ሲል የሰማነው ለምንድነው? “የዚህ ሰው ስህተቱ ምንድን ነው? ምትኑ ጌጋየ... Continue Reading →

1..2..3..

ትላንት…. ነብያት ተመኙ ከምላሳቸው ቃል ምድር ላይ 'ዲያዩ መባዘኑ ቀርቶ ባርነት አብቅቶ ተስፋ 'ዲገበዩ ግና.. ስቃያቸው በዝቶ ጽድቃቸው ዋጋ'ቶ የመርገም ጨርቅ ሆነ ኃጢአትን ተዋልደው በውርስ ተቀባብለው ነፍሳቸው ጣመነ፡፡ ያኔ.. እንባን ማበሻ የተስፋ ቀን ሲደርስ አርያም ተከፈተ በበረትም ሲገኝ ነጻነት አውጆ ሰላምን አተተ ምድር በይቅርታ በም'ረት ተከድና ፍቅር በረከተ ዛሬ…. እኒያ ደስታዎች ለታሪክ ተትተው ዘመናት አለፉ... Continue Reading →

ፈኑ እዴከ

ሠላም! እንዴት ሰነበታችሁልኝ መቼም ምስጋናዬ እጅጉን የበዛ ነው፡፡ የጦማሬ ተከታታይ ናችሁና፡፡ በምታገኟቻ ጦማሮች ላይ ያላችሁንና የተሰማችሁን ብትጽፉልኝ ደስታዬ ወደር አልባ ይሆናል፡፡ ትንሽ ጠፍቻለሁና ከይቅርታ ጋር እንኳን ለበዓለ ልደት መዳረሻ አደረሳችሁ በማለት ይቺን ጀባ ብያለሁ፡፡ ፈኑ እዴከ “በ የትውልዳችን በዘመናት ሐረግ በዛ ልመናችን ተስፋችን ቃልኪዳኑ ርቆ ባርነት ተሰጠን ጽድቃችን ድካሙ ዋጋ'ቶ የመርገም ጨርቅ ሆነ ኃጢአትን በውርስ... Continue Reading →

ምድርን የመረገጥ እምነት

ምድርን የመረገጥ እምነት Click to read in pdf ህጻኑ ከተወለደ ፮ ወር ቢሆነው ነው፡፡ ከመዳሁ ለመገላገል አንድ የዘየደውን መላ በመለማመድ ላይ ይገኛል፡፡ የአልጋ፣ የወንበር.. ሌላም ቁስ በመያዝ የመቆምና ለመሄድ የመውተርተር ፍላጎት አዕምሮውን ሞልቶታል፡፡ ስለዚህም ይጥራል አሁንም ይጥራል፡፡ በዚህ ሙከራ ውስጥ የተረዳው አንዳች እውቀት ቢኖር ጠንካራ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ነው፡፡ ምርኩዝ የሚሆነው የማይታጠፍ እጅ ወይም እቃ ካገኘ... Continue Reading →

አለሁኝ ባይ

አለሁኝ ባይ Click to Read in pdf “ ሰናይት እባላለሁ፡፡ እድሜዬና አካለ ቁመናዬ ለየትኛውም ደረጃ ይመጥናል፡፡ ብዙ ጓደኞች አሉኝ፡፡ ከአንገት፣ ከልብ፣ ከእግር…. ወዘተ የሚወዱኝና የምወዳቸው፡፡ ከቤተሰቦቼ ጋር ስሆን የምኖረው የአንድ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሰራተኛ ነኝ፡፡ ጥቂት ገላጭ የሆኑ እውነታዎች የነገርኩህ ይመስለኛልና ትረዳኛለህ ብዬ እገምታለሁ፡፡ ሰናይትን ላታውቃት ትችላለህ እንደእውነቱ እኔም አላውቅህም ብቻ በውስጤ የታፈነውን በአንድ ወቅት... Continue Reading →

ሞት ታላቅ መጽሐፍ ነው……..

ሞት ታላቅ መጽሐፍ ነው…….. Click here to read in pdf ብጹእ አቡነ ቄርሎስ በብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትሪያርክ ረፍት “ሞት ታላቅ መጽሐፍ ነው እኛ ግን አናነበውም” ማለታቸውን ተጠቅሶ ማንበቤ ለዚህ ጽሑፍ መነሻ ሆነኝ፡፡ መጽሐፍን ገልጠው ቢያነቡት እውቀትና ት/ት ይሰጣል፡፡ ትዝብትን ያካፍላል፡፡ ልምድ ይለግሳል፡፡ ምሥጢር ይገልጣል፡፡ ሕይወትን ይቀኛል፡፡ ሞትም እንዲሁ ነው ድምጹን ከሰሙት ቀለሙን ከለዩት የመጽሐፍ ያህል... Continue Reading →

Start a Blog at WordPress.com.

Up ↑