የኛ ሠፈር ፍርድ

የኛ ሠፈር ፍርድ እኛ ሠፈር ነው፡፡ አንዲት ሴትዮ በእኩለ ሌሊት እሪታዋን አቀለጠቺው፡፡ እኛም እየተንጋጋን ከቤታችን ወጣን፡፡ ሠፈርተኛው፣ የአካባቢ ጸጥታ አስከባሪዎች፣ መንገደኛው፣ የቀበሌ ሹሙ፣ ውሾቹ እንኳን ሳይቀሩ የተጮኸበት ቤት ጋ ተሰበሰቡ፡፡ ጎረምሶቹ የቤቱን በር ሰብረው ሲገቡ ባሏ ሚስቱን ውኃ ውኃ በሚያሰኝ ዱላ ይደበድባል፡፡ ጎረምሶቹ ዱላውን ነጥቀው እርሷን ከቤት አወጧት፡፡ ልብሷ ተቀዳዷል፤ የተረፈውም በደም አበላ ተጠምቋል፡፡ ከጸጥታ... Continue Reading →

ሲዳሩ ማልቀስ-አግብቶም ማልቀስ

To Read in PDF ሲዳሩ ማልቀስ-አግብቶም ማልቀስ እንኳን ለወርኃ ሚያዝያ- ወርኃ መራዊ አደረሳችሁ አደረሰን። መቼም ጊዜው የሰርግም አይደል ዘንድሮ ሚያዝያ ቢወጣብንም ቅሉ። የፈጣሪያቸው ሙሽራ ይሆኑ ዘንድ ራሳቸውን ለጃንደረባነት የለዩ ብዙዎችን አይተናል። እንደኔ አይነቱ ደግሞ “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ..” የሚለውን እያሰበ ብቻነቱን ሊረሳ ይሞሸራል፤ያገባል። ሁለቱም የተገባ ሕይወት ነውና እግዚአብሔር የልባቸውን መሻት ይሙላላቸው። ደስታን ይዛቁ-እርካታን ይሞሉ። ጋብቻ... Continue Reading →

ተ….መጽዋቹ

ተ….መጽዋቹ በየቤተ ክርስቲያኑ አጥር፣ በየመኪና መንገዱና በየመጓጓዣ ሥፍራ የልመና መስፋፋት ምን የሚያስከትል ይመስልዎታል? ለጋሽ በበዛበት ከተማ ለማኝ ቢበዛስ ምኑን ይገርማል? ለመሆኑ እርስዎ በቀን/በሣምንት ምን ያህል ለኔ ቢጤ (ለነዳይ) ይሰጣሉ? በወር ምን ያህል ወጪ ይሆንልዎታል ማለት ነው? ‘ቀኝህ ስትሰጥ ግራህ እንዳታይህ’ ስለተባለ አላውቀውም ቢሉን ጉዳያችን አልጣመዎትም ማለትን ይመስላል። መስጠቱም መድረሱም መልካም ፤ጥያቄው ግን ምን ያህል መፍትሄ... Continue Reading →

ሴንሰርሺፕ!

በነብይ መኮንን ሴንሰርሺፕ! አይጢቷ ግጥም ፃፈች፣ ርዕሱ “ድመት” የሚል “ድመት ባይርባት ኖሮ፣ አታሳድደኝም ነበር” ብላ ብዕሯን በመቀመር፡፡ ድመት ያንን አገኘች፤ “አይጥ” የሚል ርዕሱ፤ የመልስ - ምት ግጥም ፃፈች “ከአፈጣጠሯ ነው እንጂ! ድመት ጨካኝ እንዳልሆነች፡፡” የቤቱ ባለቤት ሰውየ ፣ የሁለቱን ግጥም አገኘ፣ “አሃ! ተነሱብኝ ማለት ነው!? አደጉና በኔ ላይ፣ ግጥም መፃፍ ጀመሩ? እንደተኛሁ በጭለማ፣ ነቅተው ወረቀት... Continue Reading →

ምን ዓይነት ለውጥ?

ምን ዓይነት ለውጥ? የብዙህ ሰው ሐሳብ ይመስለኛል-በውስጣችን የነበረው። ባ’ንድ ወቅት ካ’ንድ ወንድሜ ጋር ኢትዮጵያ አሁን ስላላት መልክ (ምን እንደምትመስል) ለመሳል ስንሞክር ነበር- በመስመር ሳይሆን በቃላት ጨዋታ። እርግጥ ቀላል ነው ማንኛውም ሰው ኢትዮጵያ እንዴት ሆና ልታያት ትፈልጋለህ ተብሎ ቢጠየቅ “በቴክኖሎጂና ፈጠራ የበለጸገች” “ከድህነት የተላቀቀች” “ዲሞክራሳዊ አስተዳደርና ሥርዓት የተሟሉላት..” የመሳሰሉትን መመለሱ አይቀርም። እኛም በጥቅሉ እንዲሁ ብለን ነበር።... Continue Reading →

‘የጥራት አምባሳደሮች’ ዩኒቨርስቲ ኮሌጆቻችን

‘የጥራት አምባሳደሮች’  ዩኒቨርስቲ ኮሌጆቻችን click to Read in pdf ‘የጥራት አምባሳደር’ የሚለው ሐረግ ምናልባት የቅ/ጊዮርጊስ ቢራ ማስታወቂያን ያስታውሰን ይሆናል። ጥራት የሚለው ጽንሰ ሐሳብ ሁሌም አሻሚና አነጋጋሪ ቢሆንም እንደየሙያው አግባብ ትርጓሜ ተሰጥቶት ፤ቢተገበርም ባይተገበርም ጥቅም ላይ ውሎ ይገኛል። አልኮልና ለስላሳ ድብልቅ ምሩቃን እያመረቱ የሚገኙት የትምህርት ፋብሪካዎቻችንም መፈክራቸው ይሔው ሀረግ ነው። ‘የልቀት ት/ት ቤት’ ‘ጥራት ላለው ት/ት... Continue Reading →

ትልቅ መጥበሻ

ትልቅ መጥበሻ ቆም ብለን ሰዎችን ብንመለከት እያንዳንዱ ሰው የሆነ አንድ ቦታ ተጣብቆ ያለ ነው የሚመስለው፡፡ በሕይወታቸውም ውስጥ አንዳንዴ እንዲሁ ነው፡፡ አንዳንዶች በየቤቶቻቸው ሥራዎች ተጠምደው የተጣበቁ ሲሆን፤ ከከበባቸው ሁናቴ ጋር የተጣበቁ ወይም ይቀየራል፣ ይሻሻላል፣ ወይም ይለወጣል ብለው ተስፋ ባላደረጉት ሥራ ላይ ሙጥኝ ብለው ተጣብቀው ይኖራሉ። ሌሎችም ከልምዶቻቸው ጋር ደንዝዘው በሕይወታቸው ብርሃን አልባ ድንግዝግዝ ውስጥ ተጣብቀው ይገኛሉ።... Continue Reading →

የእድገት ጣጣው

የእድገት ጣጣው አብዮታዊ እድገት Vs አብዮታዊ ልማት የየትኛው ዘመን አዝማሪ እንደነበረ ባይታወቅም እንዲህ ብሎ ገጥሞ ነበረ እኛስ መስሎን ነበር         እድገት ቀውላሎ በየቤቱ 'ሚያስር       ከሜዳ አውሎ ለካንስ ካሮት ነበረ         ሲያድግ ወደኋላ 'ሚ'በላ አሳ'ቶም           የሚጥል አውላላ፡፡ ሃገራችን ከሩጫዋና ከትግያዋ ጎን የቀራት አንድ መፈክር ያለ ይመስለኛል፡፡ ደሞ መፈክር የዘራችን አይደለምን፡፡ የቀደመውን ትተን'ኳ ከ 21... Continue Reading →

ለራስ ብቻ

(click to read pdf) ለራስ ብቻ የቀደሙ መሪዎቻቸውን ጥላና ዳና ተከትለው ይነጉዳሉ፡፡ በዚህ ወደ ተስፋ ቀዬ ለሚደረግ ጉዞ የሁል ጊዜ ትጋታቸው አብሮ ነው፡፡ ጉምም፤ ጉትልትል ማለት ነው ገብረ ጕንዳን፡፡ በረዥሙ የተስፋና የተሻለ ፍለጋ ጉዞ ብዙ ጕንዳናውያን አልቀዋል፡፡ አለቃና አዛዥ በሌለበት በዚህ ጉዞ ሁሉም ራሱን ሰጥቶ ይጓዛል፡፡ ገዢ በሌለው አነዋወራቸው ክረምቱ የችግር ዘመን ሳይመጣ በበጋ መብላቸውን... Continue Reading →

የሰልፍ ሃገሯ ወዴት ነው?

የሰልፍ ሃገሯ ወዴት ነው? ቢፒአር ሆይ ወዴት አለህ? ዘመናዊ 'ሬሽን' /ክፍፍል ተጀመረ እንዴ? (click to read in pdf ) ከሥራ ወጥቼ በሃይገር ባስ ወደቤት እየተመለስኩ ነው፡፡ ከጎኔ የተቀመጠው ወጣትና ሹፌሩ ወሬ አሙቀዋል፡፡ እኔ የጆሮዬን ቀልብ ወደነሱ ጣል እያደረኩ በዓይኔ ቀልብ ከባቢዬን እየዳሰስኩ እጓዛለሁ፡፡ “ወይ ጉድ ደ'ሞ ምን ተፈጠረ?” ወጣቱ ይጠይቃል “ጋዝ ሊገዙ ነዋ!” ሹፌሩ ይመልሳል፡፡... Continue Reading →

Start a Blog at WordPress.com.

Up ↑