ምንድነው ደስታ ?

ምንድነው ደስታ ምንድነው እርካታ ገላን ለረፍት ሰ’ቶ ህሊናን ‘ሚረታ ሠላም ዙሪያን ከቦ መንፈስ ‘ሚገዛ! ጥያቄስ ምንድነው ምንድምን ፍለጋ እድሜ ዘመን ሙሉ ላይመጣ ጥበቃ! መኖር ነው ደስታ ደስታን መሻት እርካታ ‘ምንድር’ ነው ትርጉሙ ሚታሰር ሲፈታ። ሰኔ 2004

Start a Blog at WordPress.com.

Up ↑