ሳዑዲ፡ መከራና የደም ጩኸት ከዝጎቻችን ስቃይ ጀርባ ያሉት እጆች መንግስት- 'በምእራባውያን ላይ ነብር በአረቦች ላይ ድመት'? ስቃይና እንግልት-''የችግሩ ዝቃጭ የፈጠረው ሰፈፍ'' ለስደት የጣፈው ሕዝብ? ኢትዮጵያ በታሪኳ ሁለት ጊዜ ታላላቅ ውርድት አስተናገደች፣ አንደኛው በ1977 ዐ.ም ረሃብና ቸነፈር የዓለም ህዝብ እያየው በአደባባይ ኢትዮጵያውያንን ሲያረግፍ፣ ሁለተኛው ዘንድሮ የሳዑዲ አረቢያ ሕዝብና መንግስት ዐለም እያየቸው ኢትዮጵያውያንን በአደባባይ እንደ እባብ... Continue Reading →
የዘመን ኅዳግ
Toread in pdf click የዘመን ኅዳግ መታሰቢያይሁን ዘመን ለጠፋው ዘመን ከኮሮጆው ከማደሪያው ገባ እጥፋት አበጀ ምዕቱን ከምዕት ሺህውን በሺህ አጥፍቶ ጥንተቱን አወጀ ከዘመኑ ድንበር ከማማው ላይ ቆሞ ልባሙ፡ ሕይወት እየሳለ ምልሰቱን ጀመረ “ዘመኑ ገር ሞልቶት ጥጋብ ትርጉም አ'ቶ ሰልጥኖ ነበረ ብዙዎች ተኝተው ሲያንኮራፉ ሳለ ከዚ'ች ሃገር ላይ እንቅልፍ ተሰደደ ሁሉም እየተጋ በእውቀት ሲታነጽ... Continue Reading →
ምን ዓይነት ለውጥ?
ምን ዓይነት ለውጥ? የብዙህ ሰው ሐሳብ ይመስለኛል-በውስጣችን የነበረው። ባ’ንድ ወቅት ካ’ንድ ወንድሜ ጋር ኢትዮጵያ አሁን ስላላት መልክ (ምን እንደምትመስል) ለመሳል ስንሞክር ነበር- በመስመር ሳይሆን በቃላት ጨዋታ። እርግጥ ቀላል ነው ማንኛውም ሰው ኢትዮጵያ እንዴት ሆና ልታያት ትፈልጋለህ ተብሎ ቢጠየቅ “በቴክኖሎጂና ፈጠራ የበለጸገች” “ከድህነት የተላቀቀች” “ዲሞክራሳዊ አስተዳደርና ሥርዓት የተሟሉላት..” የመሳሰሉትን መመለሱ አይቀርም። እኛም በጥቅሉ እንዲሁ ብለን ነበር።... Continue Reading →
የሰልፍ ሃገሯ ወዴት ነው?
የሰልፍ ሃገሯ ወዴት ነው? ቢፒአር ሆይ ወዴት አለህ? ዘመናዊ 'ሬሽን' /ክፍፍል ተጀመረ እንዴ? (click to read in pdf ) ከሥራ ወጥቼ በሃይገር ባስ ወደቤት እየተመለስኩ ነው፡፡ ከጎኔ የተቀመጠው ወጣትና ሹፌሩ ወሬ አሙቀዋል፡፡ እኔ የጆሮዬን ቀልብ ወደነሱ ጣል እያደረኩ በዓይኔ ቀልብ ከባቢዬን እየዳሰስኩ እጓዛለሁ፡፡ “ወይ ጉድ ደ'ሞ ምን ተፈጠረ?” ወጣቱ ይጠይቃል “ጋዝ ሊገዙ ነዋ!” ሹፌሩ ይመልሳል፡፡... Continue Reading →
ሞት ታላቅ መጽሐፍ ነው……..
ሞት ታላቅ መጽሐፍ ነው…….. Click here to read in pdf ብጹእ አቡነ ቄርሎስ በብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትሪያርክ ረፍት “ሞት ታላቅ መጽሐፍ ነው እኛ ግን አናነበውም” ማለታቸውን ተጠቅሶ ማንበቤ ለዚህ ጽሑፍ መነሻ ሆነኝ፡፡ መጽሐፍን ገልጠው ቢያነቡት እውቀትና ት/ት ይሰጣል፡፡ ትዝብትን ያካፍላል፡፡ ልምድ ይለግሳል፡፡ ምሥጢር ይገልጣል፡፡ ሕይወትን ይቀኛል፡፡ ሞትም እንዲሁ ነው ድምጹን ከሰሙት ቀለሙን ከለዩት የመጽሐፍ ያህል... Continue Reading →
ለእግረኛ የተከለከለ
ለእግረኛ የተከለከለ ፎቶ ማንሳት የተከለከለ ነው፡፡ መግባት የተከለከለ፡፡ ማየት የተከለከለ መናገር የተከለከለ ማድመት የተከለከለ መንዳት የተከለከለ ማቆም የተከለከለ መቀመጥ የተከለከለ…. ወዘተ ብዙ የተከለከሉዎች፡፡ የሕብረተሰባችን የአኗኗር ህግ በብዙ ክልከላዎች የተሞላ ነው፡፡ እናትና አባት 'አታድርግ' የሚል የክልከላ ህግ አለው፡፡ አካባቢው 'አስነዋሪ' የሚል መከልከያ ያወጣል፡፡ ቀበሌ ባለሥልጣን መንግስት ብዙ የክልከላ ህጎች አሏቸው፡፡ በሰው በራፍ /ደጅ/ ላይ እንዳይቀመጡ የተቃጠለ... Continue Reading →