የዘመን ኅዳግ

  Toread in pdf click የዘመን ኅዳግ    መታሰቢያይሁን ዘመን ለጠፋው ዘመን ከኮሮጆው ከማደሪያው ገባ እጥፋት አበጀ ምዕቱን ከምዕት ሺህውን በሺህ አጥፍቶ ጥንተቱን አወጀ ከዘመኑ ድንበር ከማማው ላይ ቆሞ                      ልባሙ፡ ሕይወት እየሳለ ምልሰቱን ጀመረ “ዘመኑ ገር ሞልቶት ጥጋብ ትርጉም አ'ቶ ሰልጥኖ ነበረ ብዙዎች ተኝተው ሲያንኮራፉ ሳለ ከዚ'ች ሃገር ላይ እንቅልፍ ተሰደደ ሁሉም እየተጋ በእውቀት ሲታነጽ... Continue Reading →

ምንድነው ደስታ ?

ምንድነው ደስታ ምንድነው እርካታ ገላን ለረፍት ሰ’ቶ ህሊናን ‘ሚረታ ሠላም ዙሪያን ከቦ መንፈስ ‘ሚገዛ! ጥያቄስ ምንድነው ምንድምን ፍለጋ እድሜ ዘመን ሙሉ ላይመጣ ጥበቃ! መኖር ነው ደስታ ደስታን መሻት እርካታ ‘ምንድር’ ነው ትርጉሙ ሚታሰር ሲፈታ። ሰኔ 2004

መድኃኒት

ሆሣዕና በአርያም!  ሆ..ሣ.ዕና በአ…ር.ያም! በአርያም በልዕልና ጸንቶ የሚኖር ከአርያም የተገኘ መድኃኒት ማለት ነው። እምሆሣዕናሁ (መድኃኒት ከመሆኑ የተነሣ) አርአየ ተአምረ ወመንክረ-- ፍጹም ተአምራቱን ገለጸ አእምሮ ጠባይ ያልቀናላቸውን ሕፃናት አእምሮ ጠባይ ቀንቶላቸው፤ ንባበ አእምሮ ለሌላቸው አዕባን ንባብ አእምሮ ሰጥቶ እንዲያመሰግኑት አድርጓል። ግትነቱን ገልጦ።  አርአየ ጸጋ ወኃይለ-- ከሥልጣኑ ሳይለይ በጽርሐ አርያም በዘባነ ኪሩብ ባለ በምድር ልጅነትን ከሃሊነትን ገለጸ።... Continue Reading →

ሴንሰርሺፕ!

በነብይ መኮንን ሴንሰርሺፕ! አይጢቷ ግጥም ፃፈች፣ ርዕሱ “ድመት” የሚል “ድመት ባይርባት ኖሮ፣ አታሳድደኝም ነበር” ብላ ብዕሯን በመቀመር፡፡ ድመት ያንን አገኘች፤ “አይጥ” የሚል ርዕሱ፤ የመልስ - ምት ግጥም ፃፈች “ከአፈጣጠሯ ነው እንጂ! ድመት ጨካኝ እንዳልሆነች፡፡” የቤቱ ባለቤት ሰውየ ፣ የሁለቱን ግጥም አገኘ፣ “አሃ! ተነሱብኝ ማለት ነው!? አደጉና በኔ ላይ፣ ግጥም መፃፍ ጀመሩ? እንደተኛሁ በጭለማ፣ ነቅተው ወረቀት... Continue Reading →

1..2..3..

ትላንት…. ነብያት ተመኙ ከምላሳቸው ቃል ምድር ላይ 'ዲያዩ መባዘኑ ቀርቶ ባርነት አብቅቶ ተስፋ 'ዲገበዩ ግና.. ስቃያቸው በዝቶ ጽድቃቸው ዋጋ'ቶ የመርገም ጨርቅ ሆነ ኃጢአትን ተዋልደው በውርስ ተቀባብለው ነፍሳቸው ጣመነ፡፡ ያኔ.. እንባን ማበሻ የተስፋ ቀን ሲደርስ አርያም ተከፈተ በበረትም ሲገኝ ነጻነት አውጆ ሰላምን አተተ ምድር በይቅርታ በም'ረት ተከድና ፍቅር በረከተ ዛሬ…. እኒያ ደስታዎች ለታሪክ ተትተው ዘመናት አለፉ... Continue Reading →

ፈኑ እዴከ

ሠላም! እንዴት ሰነበታችሁልኝ መቼም ምስጋናዬ እጅጉን የበዛ ነው፡፡ የጦማሬ ተከታታይ ናችሁና፡፡ በምታገኟቻ ጦማሮች ላይ ያላችሁንና የተሰማችሁን ብትጽፉልኝ ደስታዬ ወደር አልባ ይሆናል፡፡ ትንሽ ጠፍቻለሁና ከይቅርታ ጋር እንኳን ለበዓለ ልደት መዳረሻ አደረሳችሁ በማለት ይቺን ጀባ ብያለሁ፡፡ ፈኑ እዴከ “በ የትውልዳችን በዘመናት ሐረግ በዛ ልመናችን ተስፋችን ቃልኪዳኑ ርቆ ባርነት ተሰጠን ጽድቃችን ድካሙ ዋጋ'ቶ የመርገም ጨርቅ ሆነ ኃጢአትን በውርስ... Continue Reading →

ነሽ ለእኔ!

  ነሽ ለእኔ! የእውነት ጥጋት…. መገኛ የእኔነት ስሜት ….መናኛ የሕይወት ነጥብ…. ምልክት ያንቺነት ለ'ኔ……ተምሳሌት ነሽ ለ'ኔ… ነጥቤ የማትጠፊ ከህልም ካ'ሳቤ ነሽ ለ'ኔ… ቀለሜ የእውቀት ባህር መቅድሜ እማይ! የሕይወት ኑሮ ጣዕሜ!!

ያልሞተው ሟች

(CLICK HERE TO READ IN PDF)ያልሞተው ሟች ቅድመ አግድም…… ከቁሙ አፈር ላይ አፈር አልባ ወዙ ተራ ላብ እንዳይሆን ጨው ጨምሮበት ለቁልሉ አፈር ጣይሙን 'ዲጣፍጥ ሕይወት 'ዲዘራ ወዙን ቢቀዳለት አፈር ውኃ ወሰደው አፈር አፈር በላው 'ሚሉት ትርጓሜ ዘመኑ አለፈ ሲፈጠር ከአፈር ሲፈርስ ወደአፈር እርባን የለሽ ትረጉም የቀድሞ ታጠፈ፡፡ አፈር ወዝ አውጥቶ አፈር ላይ ሲጨመር የወዙ መዓዛ... Continue Reading →

የትዳር ገጾች

የትዳር ገጾች የህይወት እንቆቅልሽ ለመፍታት አጋር ረዳት መፈለጉ ከአቻ ተጓዳኝ ጋር መጣመር ከብቻ ህይወት ማፈግፈጉ ምኑ ላይ ነው ወጉ? ያለመተማመን ቅመም የበዛበት የመውደድ ሽታ 'የታጠኑ ለአብሮነት ህይወት ማዕድ ከአንድ ገበታ መስፈኑ ምንድር ነው እርባኑ? እኔነትን ከፍሎ ለተሰጠው የ'ርሱነትን ጣእም ማጣጣሙ መተሳሰብ ባልከበረበት ለአንድነት ኑሮ መታመሙ ምን ይሆን ጥቅሙ? ስሜትን መካፈል ያልነገሰበት የጥምረት ካባ መደረቡ ክብርን... Continue Reading →

Start a Blog at WordPress.com.

Up ↑