ምስል አልባ ፊደላት እይታው እንዲህ ነው….. ቋሚው አዘንብሏል ውስጡ ተቦረትፎ ማገሩም ተመዟል ግድጊዳው ተምሶ የቀለም ድርቅ መቶት አፈር አፈር ሆኗል ጣራው ጨቅይቶ ጽልመት ተላብሶ እይታን ተነፍጓል ደጁ 'ደርሻ ታርሶ ተኮትኩቷል ለቁሻሻ ተክል በሩ.. መዝጊያነቱ ቀርቶ መከለያ ሆኗል ለመዝጋ ቢታሰብ ከጩኸቱ፣ ከትግያ በላይ አቅሙ ይታጎላል ቀንም ሆነ ማታ ጭለማ ተውጦ ዓመታት ተቆጥሯል፡፡ አዎ! ጎረቤቱ ብዙ... Continue Reading →
ያልሞተው ሟች
( click to read pdf) ቅድመ አግድም…… ከቁሙ አፈር ላይ አፈር አልባ ወዙ ተራ ላብ እንዳይሆን ጨው ጨምሮበት ለቁልሉ አፈር ጣይሙን 'ዲጣፍጥ ሕይወት 'ዲዘራ ወዙን ቢቀዳለት አፈር ውኃ ወሰደው አፈር አፈር በላው 'ሚሉት ትርጓሜ ዘመኑ አለፈ ሲፈጠር ከአፈር ሲፈርስ ወደአፈር እርባን የለሽ ትረጉም የቀድሞ ታጠፈ፡፡ አፈር ወዝ... Continue Reading →
እድሜ ዘመን ቁጥር
እድሜ ዘመን ቁጥር ህልውናዬ ጸድቆ እስትንፋስን ስ'ቸር እኩል ዘመን ሰፈርን እድሜዬና ምድር እሷ ……. የዓመት ትግሏን ጨርሳ በወቅት ስትከፈል ከጽጌ 'ቅፍ ገብታ ድካሟ ተረስቶ መንፈሷ ታድሷል እድፍ ገላዋ ነጽቶ ባ'ዲስ ልብስ ሸብርቋል ይኽን ትቆጥራለች…………. አንድ ሁለት እያለች፡፡ እኔ………. ፍላጎቴ በዝቶ መልኬ ተቀይሯል ሥጋዬ ጀግኖ ዓለሙ ጠቦኛል እኔም እቆጥራለሁ…….. አንድ ሁለት እላለሁ የእድሜዬን ወረት ባዶ እያስቀረሁ፡፡... Continue Reading →
እንደ መግቢያ
አለማወቅ መልካም ፪ ከአውቃለሁ እውቀቱ አለማወቁን ካወቀው ያ………. አ'ለማወቅ መልካም ነው!! የካቲት ፳፻ዓ.ም አዲስ አበባ