መጪው ጊዜ ከዐብይ ጋር!

መንግሥት በሽብርተኝነት ለፈረጃቸው ተቃዋሚ ቡድኖች የሽብርተኝነት ፍረጃውን በማንሳት ትልቅ ርምጃ ወስዷል፡፡ ጸረ-ሽብር ሕግ አንስቶ የምህረት አዋጅ አጽድቋል፡፡ ይህንኑ ርምጃ ተከትሎ በሽብር ተከሰው የነበሩ ፖለቲካ ቡድኖች ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ ጥሪ አድርጓል፡፡ በሌላ በኩል ብሄርተኞች የክልልነት፣ የሙስሊም መብት ተሟጋቾች ደሞ ነባር ጥያቄያቸውን እያሰሙ ያሉት ለውጡን ለመጠቀም ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደሞ በውጭ ሀገራት ያሉ የተቃራኒ ፖለቲካ ቡድኖች ጠቅላይ ሚንስትሩ ያቀረቡትን ጥሪ ተቀብለው ወደ ሀገር መግባታቸውን በበጎ የሚያዩት እንዳሉ ሁሉ በስጋት የሚያዩትም ወገኖች አልጠፉም፡፡ እናም ቡድኖቹ ተቃራኒ ፍላጎቶቻቸውን እና ፖለቲካዊ አጀንዳዎቻቸውን በምን መልኩ ያንጸባርቁ ይሆን? ቡድኖቹ ባንድ ጊዜ መሰባሰባቸው ለሀገሪቷ ምን ዐይነት ትሩፋት እና ስጋት ይፈጥር ይሆን? ሁኔታው በጠቅላላው ምን ዐይነት ቅራኔዎችን እና ግጭቶችን ሊፈጠር ይችላል?

ዶ/ር አብይ አህመድ ከኃይለማርያም ደሳለኝ በምን ይለያሉ?

በተለይ ዶክተር አብይ እንደ አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሁሉ የግንባሩ አስኳል ከሆነው ሕወሃት ውጭ የተመረጡት ስለሆኑ ለሩብ ክፍለ ዘመን ጭቆና የመረረውን ሕዝብ ወደ ቃል ኪዳኗ ምድር የሚያደርሱ ሐዋሪያ አድርጎ ማየት በምንም መልኩ የሚያዋጣ አይደለም፡፡

ኦቦ ለማና ህወሃት

አቶ ለማ መገርሳ የመንግስት ባለስልጣን ሆኖ በቆየበት ጊዜ ሁሉ ሲያስገድል፣ በሀሰት ሲያስወነጅል፣ ሕዝብን ከሕዝብ ሲያባላ እና በድህነት እንድንሰቃይ ለሙስና ሲያጋፍር ነው የኖረው። ሌላውን የኢህአዴግ ባለስልጣን አስኮንኖ፣ አቶ ለማ እና ዶ/ር ዐብይን ነጻ የሚያስወጣ ምንም ዓይነት ምክንያት የለንም። ማሽሞንሞን ሳያስፈልግ፥ አቶ ለማ መገርሳ የኢህአዴግ ሽንት ጨርቅ ነው። የአምባገነን ስርዓት ሽንት እንዳይታይ በማድረግ ረገድ የሚጫወተው የዳይፐርነት ሚና... Continue Reading →

ከደርግ ወደ ጎሣዊ ደርግ- “ግንቦት 20” (ክፍል ፬)

የመንግስት ውሸትና የሃይማኖት ተቋማት ውድቀት የትግራይ ሕዝብ “ነጻ አውጡኝ” ብሎ ሳይሰይማቸው፣ ሳይመርጣቸው፣ ሳይጠይቃቸው፣ ራሳቸውን “የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር” ብለው የሰየሙ ወንበዴዎችና ሽፍቶች የምኒልክ ቤተመንግሥት ከገቡ 26 ዓመታት ተቆጥረዋል። በቂም፣ በበቀል፣ በክፋትና በኢሞራላዊ ተግባራት የተሞሉ፤ ኢትዮጵያዊ መሆናቸው ፈጽሞ የሚያጠራጥር፤ ማንነታቸው ይህ ነው ተብሎ የማይታወቅ፤ በሐሰት ስም ከበረሃ እስከ ቤተመንግሥትና ዓለምአቀፍ መድረክ ላይ የታዩ፤ በሐሰት ፕሮፓጋንዳ... Continue Reading →

ከደርግ ወደ ጎሣዊ ደርግ- “ግንቦት 20” (ክፍል ፫)

ስደት በመጀመሪያው ከደርግ ወደ ጎሣዊ ደርግ- “ግንቦት 20” (ክፍል ፩) ጽሑፍ ከ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች መሃል ስለከሸፈው የፌዴራል ሥርዓት እና የትምህርት ፖሊሲው ክስረት ማተታችን ይታወሳል። በሁለተኛው ክፍል ሰለ መሬት ነጠቃ አስነብበናል በዚህኛው ክፍል ሁለት ደግሞ የአፓርታይዳዊ አገዛዝ አራማጁ ህወሓት ሥልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ከዘራቸው በርካታ መርዛማ ፍሬዎች መካከል ቀጣዩን ከማሳያዎች ጋር ማስነበባችን እንቀጥላለን። መርዛማ ፍሬ 4፡ ስደት የኢትዮጵያዊያን... Continue Reading →

“ህወሃት በሚያኮርፍባቸው የሶማሊያ ‹አሸባሪ› ድርጅቶች ይጠረጠራል”

“ህወሃት በሚያኮርፍባቸው የሶማሊያ ‹አሸባሪ› ድርጅቶች ይጠረጠራል” የጸጥታ ስጋት ከድጎማ መቀነስ ጋር ይያያዛል? ሰሞኑን በከፍተኛ ደረጃ የዓለም መገናኛዎች ርዕስ የኢትዮጵያ ሰራዊት ከሶማሊያ ለቆ የመውጣቱ ጉዳይ ነው። የሶማሊያ ባለሥልጣናት ስለጉዳዩ የተነገራቸው አንዳችም ነገር እንደሌለ መግለጻቸው፣ አልሸባብም የሠራዊቱን እግር እግር እየተከተለ የተነጠቃቸውን ወረዳዎች መቆጣጠሩና ኢህአዴግ ጉዳዩን ያስተባበለበት አግባብ ጎልጉል የመረጃ አቀባዮቹን እንዲያነጋግር መነሻ ሆኗል። እንደ መረጃ ሰዎቹ ከሆነ በስም ተለይቶ... Continue Reading →

አዲስ አበባ ተቆላልፋለች

አዲስ አበባ ተቆላልፋለች ፖሊስ እና ሰራዊቱ በሕዝብ ላይ አልተኩስም ብለዋ ወቅታዊ ሪፖርታዥ በሳምንቱ መግቢያ የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ብሄራዊ እርቅ እና ድርድር እንዲደረግ ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል። አምስቱ የሕወሃት ቁንጮዎች ትእቢት የተሞላበት ምላሽ ነው የሰጡት። ከድርድር ይልቅ ከሕዝብ ጋር ጦርነት መግጠምን መርጠዋል። አብዛኛው የፖሊስ እና የሃገር መከላከያ ሰራዊቱ “ሕዝብ ላይ አልተኩስም” ማለታቸው የህወሃት አመራርን ጭንቅ ውስጥ አስገብተውታል።... Continue Reading →

የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጉዞ…

የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጉዞ… (ክንፉ አሰፋ) July 21, 2015  ክንፉ አሰፋ “…ከዚህ በኋላ ህዝብ ሰብስቦ ማውራት ላቆም ነው። ጊዜው ተቀይሯል። ትግል ለደካማ መንፈስ አይሆንም። ትግል መውደቅን ይጠይቃል። ሲወድቁ ግን ለመነሳት መሞከርን ይጠይቃል። ስንወድቅ ልታዩን ትችላላችሁ ስንነሳ ግን ታዩናላችሁ … ” ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ይህንን የተናገሩት የአስመራ ጉዟቸው ከመሰማቱ ጥቂት ቀናት በፊት ነበር። ንግግሩ ለብዙዎች ግርታ... Continue Reading →

Start a Blog at WordPress.com.

Up ↑