ከደርግ ወደ ጎሣዊ ደርግ- “ግንቦት 20” (ክፍል ፮)

የአንድ ጎጥ የበላይነትና የመበታተን አደጋ! ራሳቸውን “የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር” ብሎ በመሰየም የትግራይን ሕዝብ ሽፋን በማድረግ፤ “የምታገለው ለአንተ ነጻነት ነው” በማለት፤ መልሶ እታገልለታለሁ ያለውን ሕዝብ ያስጨፈጨፈው፣ ያስራበው፣ የግፈ ሰለባ ያስደረገው፣ … ራሱን ህወሓት እያለ የሚጠራው የወንበዴዎች ቡድን የኢትዮጵያን የሥልጣን መንበር ከተቆናጠጠ በኋላ የትግራይ ሰዎችን በሌላው ኢትዮጵያዊ ለማስጠላትና “ስም ለማሰጠት” እንዲሁም ለማጠልሸት ባለፉት 26ዓመታት ሲሰራ... Continue Reading →

ከደርግ ወደ ጎሣዊ ደርግ- “ግንቦት 20” (ክፍል ፬)

የመንግስት ውሸትና የሃይማኖት ተቋማት ውድቀት የትግራይ ሕዝብ “ነጻ አውጡኝ” ብሎ ሳይሰይማቸው፣ ሳይመርጣቸው፣ ሳይጠይቃቸው፣ ራሳቸውን “የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር” ብለው የሰየሙ ወንበዴዎችና ሽፍቶች የምኒልክ ቤተመንግሥት ከገቡ 26 ዓመታት ተቆጥረዋል። በቂም፣ በበቀል፣ በክፋትና በኢሞራላዊ ተግባራት የተሞሉ፤ ኢትዮጵያዊ መሆናቸው ፈጽሞ የሚያጠራጥር፤ ማንነታቸው ይህ ነው ተብሎ የማይታወቅ፤ በሐሰት ስም ከበረሃ እስከ ቤተመንግሥትና ዓለምአቀፍ መድረክ ላይ የታዩ፤ በሐሰት ፕሮፓጋንዳ... Continue Reading →

ከደርግ ወደ ጎሣዊ ደርግ- “ግንቦት 20” (ክፍል ፫)

ስደት በመጀመሪያው ከደርግ ወደ ጎሣዊ ደርግ- “ግንቦት 20” (ክፍል ፩) ጽሑፍ ከ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች መሃል ስለከሸፈው የፌዴራል ሥርዓት እና የትምህርት ፖሊሲው ክስረት ማተታችን ይታወሳል። በሁለተኛው ክፍል ሰለ መሬት ነጠቃ አስነብበናል በዚህኛው ክፍል ሁለት ደግሞ የአፓርታይዳዊ አገዛዝ አራማጁ ህወሓት ሥልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ከዘራቸው በርካታ መርዛማ ፍሬዎች መካከል ቀጣዩን ከማሳያዎች ጋር ማስነበባችን እንቀጥላለን። መርዛማ ፍሬ 4፡ ስደት የኢትዮጵያዊያን... Continue Reading →

ከደርግ ወደ ጎሣዊ ደርግ- “ግንቦት 20” (ክፍል ፪)

የመሬት ነጠቃ በረዥሙ የኢትዮጵያ ታሪክ በአስተዳደሩ ተመስግኖ በክብር የተሸኘ ገዥ ስለመኖሩ የሚያወሳ ታሪከ-ድርሳን ፈልጎ ማግኘት የሚቻል አይመስልም። ሁሉም አገዛዞች የተወገዱት በአመፅ አልያም በተፈጥሮ ሞት ነው። ልክ የዛሬ 26 ዓመት 1983 ዓ.ም. ወርሃ ግንቦት በምዕራቡ አለም ረዳትነት በጠመንጃ ወደ ሥልጣን የመጣው አፓርታይዳዊው የህወሓት ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ በቀደሙት ገዥዎች የብረት ጫማ ውስጥ ተከልሎ አፈናና ግድያውን “ግፋ በለው!”... Continue Reading →

ከደርግ ወደ ጎሣዊ ደርግ- “ግንቦት 20” (ክፍል ፩)

ፌዴራሊዝምና የትምህርት ፖሊሲ ግንቦት ሃያ ባይኖርስ ኑሮ፥ የደርግ ዘመን ቀጥሎ ቢሆን ኑሮ ላልፉት ሩብ ምዕት ዐመታት ኢትዮጵያ ምን ትመስል ነበር እያልኩ አስባለው። የግንቦት ሃያ ህልም ቅዠት በነበረ፥ ባለቁምጣዎች ቤተ መንግስትን ለመቀመጫቸው የ''ሰፊውን ሕዝብ'' ንብረት ለጎፈሬያቸው ማስዋቢያ ባያደርጉት በነበረ፥ የሃያ ስድስት ዓምት ጆሮአችን በከሳ ኑሮ- ከአደንቁሩ ፕሮፓጋንዳ እያልኩ እያያሰላሰልኩ ሃሳቤን ከማስፈሬ አስቀድሞ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የሠራውን ዘጋባ... Continue Reading →

የግንቦት ፍሬዎች ሁለት

የግንቦት ፍሬዎች ሁለት To Read in PDF ዘመነ ግንቦታውያን ከሰጡን ፍሬዎች መቅመስ ጀምረናል። የጎልማሳው ትውልድና የተተኪው ትርክት እንደቀጠለ ነው። ከፍሬዎቹ አንዱ በሆነው የዜግነት ክብር ላይ ዛሬ እንቆያለን። ከዚህ ቀደም በዚህ ርእስ ላይ ጽፌ ነበር። ይሄኛው ጽሑፍ ዝርዝር ዜናሁ ነው። ሰው በመሆን ጸጋና በጥቅሙ ደስታ አንድ ሆነን ተሰርተናል። በምንኖርበት ሥፍራ ባስቀመጥናቸውና በተቀመጡብን አለቃዎች ምክንያት ይህ የሰውነት... Continue Reading →

የግንቦት ፍሬዎች

የግንቦት ፍሬዎች የግንቦት ወር ተለይቶ የሚታወቀው ፀሓያማ ወር በመሆን ነበር። የመስከረምን ድርሻ ከነጠቀ በኋላ ግን ዝነኛና የማይረሳ አዚማም እና ተስፋ ፈንጣቂ ወር በመሆን ተገልጧል። አሁን ግን ብዙን ነገር ተቀያይሯል ከሩብ ምዕት ዓመት በኋላ የአንድ ትውልድ ዘመን ጎልምሶ ሌላኛው ተተኪ ትውልድ እየበቀለ ይገኛል። ለእኒህ ትውልዶች ታሪካቸው ግንቦትን በወራት ሁሉ ላይ ነግሦ ሲንገዋለል ከትቦታል። የብር ኢዮቤልዩ (ሃያ... Continue Reading →

ግንቦት ሃያ ለማን?

ግንቦት ሃያ ለማን? 23 ዐመት ከፊት ወይስ ከኋላ ተተኪ ወይስ አካኪ የምናውቀው መንግስት እና የማናውቀው ከየካቲት ወደ መስከረም ከመስከረም ወደ ግንቦት የተሻገረው የበዓል ታሪካችን ከግንቦት ጋር የተጣበቀበትን 23ኛ በዐሉን ሽርጉድ ብሎ እያከበረ ነው፡፡ እንዳያልፉት የለም ያዘመን አለፈ በቀን ሦስቴ 'መብላት ህልም እየነፈሰ ድኅነት ተረቶ ነፍስ እየመለሰ¡¡ ከግንቦት 83 በኃላ የተወለዱት 23ኛ ዓመታቸውን ሲያከብሩ ሌሎች ለትምህርት... Continue Reading →

Start a Blog at WordPress.com.

Up ↑