ዐይናችን ተከፍቷል ህሊናችን ነቅቷል

ዐይናችን ተከፍቷል ህሊናችን ነቅቷል ከአንተነህ መርዕድ የመጀመርያው የኬንያ ፕሬዝደንትና የነፃነት ታጋይ ጆሞ ኬንያታ ብዙ ጊዜ የሚጠቀስላቸው፣ ስለ ቅኝ ገዥዎች የተናገሩት እውነት ይህን ይመስል ነበር። “ሚሲዮኖች ወደ አፍሪካ ሲመጡ እነሱ መጽሃፍ ቅዱስ፤ እኛ ደግሞ መሬት ነበረን። ዐይናችንን ጨፍነን እንዴት እንደምንጸልይ አስተማሩን። ዐይናችንን ስንገልጠው ግን እነሱ መሬታችንን እኛ መጽሃፍ ቅዱሱን ታቅፈናል” አሉ። “When the Missionaries arrived, the... Continue Reading →

የሰው ዘር ጭፍጨፋ በአዲስ አበባ

የሰው ዘር ጭፍጨፋ በአዲስ አበባ   (ጥበቡ በለጠ) በየአመቱ የካቲት 12 ቀን ሲደርስ ከማስታውሳቸው የዚህች አገር ባለውለተኞች መካከል ተመስገን ገብሬ አንዱ ነው። ይህ ሰው ሀገሩ ኢትዮጵያ በፋሽስቶች እንዳትወረር ብዙ ትግል አካሂዷል። ከወረራው በኋላም በአርበኝነት ተሰማርቶ የፋሽስቶችን ግብአተ-መሬት ካፋጠኑ የኢትዮጵያ ታላላቅ ደራሲያን መካከል ከግንባር ቀደሞቹ አንዱ ነው። ተመስገን ገብሬ በ1901 ዓ.ም ጐጃም ደብረማርቆስ ከተማ ነው የተወለደ።... Continue Reading →

አዲስ አባባ ስለምን ታወዛግባለች? (ዘላለም ክብረት)

አዲስ አባባ ስለምን ታወዛግባለች? (ዘላለም ክብረት) Zone 9 ሕሩይ ሚናስ አስደናቂ ሰው ነው፡፡ የገበሬ ልጅ፣ በአስራዎቹ መጨረሻ አዲስ አበባ የገባ፡፡ ከዛም የአብነት ተማሪ ሆነና ቅዳሴና ቅኔ ሞካከረ፡፡ እሱ አልሆን ሲለው ጎዳና ወጥቶ ጎዳና አዳሪ ሆነ፡፡ ቀጠለና የለማኝ መሪ (sighted guide) ሆነ፡፡ እሱም ሲያልፍ ‹ለምን አልማርም?› ብሎ ትምህርት ተማረና ዩንቨርሲቲ በገባ በዓመቱ ‹ማርክሲስት› ሆነ፡፡ ትምህርቱንም ለአቢዮቱ... Continue Reading →

በታጋዮች ክንድ የደቀቀው ፍርድ

በታጋዮች ክንድ የደቀቀው ፍርድ – ታሪኩ አባዳማ ታጋዩ አቶ በረከት ስምኦን ሲኖሩበት ከነበረ ንብረትነቱ የአቶ መሀሪ ተወልደ ብርሀን የሆነ የተንጣለለ ቪላ ለቀው እንዲወጡ እና ለባለንብረቱ እንዲያስረክቡ ፍርድ ቤት ቢወስንም ለሳቸው የሚመጥን ሌላ ቤት ባለመገኘቱ ውሳኔው ተፈፃሚ ሊሆን አልቻለም። ቤቱ ለባለንብረቱ እንዲመለስ ላለፉት ስምንት አመታት በተከታታይ በህግ ቢወሰንም ከህግ በላይ የሆነ ሰው ስለሚኖርበት ተፈፃሚ አልሆነም –... Continue Reading →

ኢትዮጵያ በሁለቱም ጫፍ የምትቃጠል ሻማ እንዳትሆን

ኢትዮጵያ በሁለቱም ጫፍ የምትቃጠል ሻማ እንዳትሆን ያንዲት አገር ዜጎችን በዘር ሸንሽኖ በወርቅ እና በነሀስ መፈረጅ ብሎም ከዚህ ፖሊሲ በመነጨ ኢኮኖሚውን ፣ መገናኛ አውታሩን ፣ መከላከያውን ፣ ቁልፍ የመንግሰት ስልጣን ብሎም አጠቃላይ የፖለቲካ ህይወት ከዚያ ‘ወርቅ’ ብሎ ከሸነገለው ዘር ተመርጦ በተመለመለ ሀይል ሙሉ ቁጥጥር ስር እንዲውል ማረጋገጥ የለየለት የህገወጥ መንግሰት ባህሪ መሆኑን የሚያረጋግጥ ታሪካዊ ወቅት ላይ... Continue Reading →

ለወያኔ ድርጊት፣ ምን ስም እናውጣለት

ለወያኔ ድርጊት፣ ምን ስም እናውጣለት (ይገረም ዓለሙ) ወገንን ጨፍጫፊ ቆዳው የነጣ ነው በአበሻ የሚጨክን ፈረንጅ ብቻ ነው፤ እያለ የሚያስብ የዋህ ፍጡር ማነው ጨፈጫፊ ከሆነ አበሻም ጣሊያን ነው እንቶኔም በተግባር ሲኞር እንቶኔ ነው፤ በየግዜው እየከፋ የሄደውን የወያኔ አረመኔነትና የሀገራችንን ጉዞ ወዴትነት ሳስብ ትውስ ያለችኝን ይህችን ስንኝ ወደ ማስታወሻየ ገልብጬ ያኖርኳት በ1980ዎቹ መጨረሻ ግድም ለንባብ ይበቁ ከነበሩት... Continue Reading →

የመንግስት ብክነት፡ በቢሊዮንና በሚሊዮን—–

ዮሃንስ ሰ. አዲስ አድማስ • የመንግስት ኤሌክትሪክ፡ በአመት ከ6 ቢ. ብር በላይ ያከስረናል • የሆቴልና ቱሪዝም ማሰልጠኛ ማዕከል፤ የ5 ሚሊዮን ብር ‘አስደናቂ ድራማ’ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ እንደ ኡጋንዳ ቢሻሻል፣... በአመት 6 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ሃብት መፍጠር ይቻል ነበር ይላል፣ የአለም ባንክ ያወጣው አዲስ ሪፖርት። እንደ ጋና ማሻሻል ደግሞ ከዚያ የበለጠ ጥቅም ያስገኛል። የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት፣... Continue Reading →

ለወቅታዊው የሃገሪቷ ቀውስ 7 የመፍትሄ ሃሳቦች

ለወቅታዊው የሃገሪቷ ቀውስ 7 የመፍትሄ ሃሳቦች ስንገድለው ስንደበድበው . . . . አምቦ ብቻ አይደለም ፥ በአምቦና በአዲስ መካከል ያለችው ቡራዩም የተቃውሞ አውድማ ሆናለች። ሱሉልታ፣ ሆለታ፣ ሰበታም አልጸዱም። አዲስ አበባ አፍንጫ ላይ ያሉትን አገዛዝ ማረጋጋት ካልቻለ፣ እንደ ዶዶላ፣ ባኮ፣ ነጆ፣ ቆቦ . . . . ያሉትን እንዴት ነው የሚያረጋጋው? በጉልበት፣ በኃይል ይሄን ኣይነት እኔ በእደሜዬ... Continue Reading →

ማስተር ፕላኑና ተቃውሞው……….የፖሊሲ ግድፈቶችና የመፍትሄ ሀሳብ!

                ማስተር ፕላኑና ተቃውሞው              የፖሊሲ ግድፈቶችና የመፍትሄ ሀሳብ! የሰሞኑ ርህራሄ የጎደለው የመንግስት እርምጃን የሚያሳዩ ዜናዎችና ምስሎችን ማየት እጅጉን ያማል፡፡ ገዢዎቻችን የህዝብን ቅሬታ በጠረጴዛ ዙሪያ መፍታት የሚባል ነገር ከራቃቸው ሰነባብተዋል፡፡ በውይይት ከያዙት አቋም የተመለሱበት ጊዜያት ጥቂት ቢሆንም፣ ከህዝብ ተቃውሞ ሲነሳ ተወካዮችን በማስመደብ እና ሽማግሌዎችን በመላክ ድርድሮችና ውይይቶች ይደረጉ የነበሩበት ጊዜ ሩቅ አይደለም፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ... Continue Reading →

የተራበች ኢትዮጵያ

የተራበች ኢትዮጵያ (አንተነህ መርዕድ) በሞት አፋፍ ላይ ቀናቸውን በፀጋ የሚጠባበቁ የሰማንያ አምስት ዓመት ካናዳዊ አዛውንት የስቃይ ማስታገሻ መድሃኒታቸውን እየሰጠኋቸው እያለ “ከየት አገር ነህ?” ሲሉ ጠየቁኝ በደከመ አንደበታቸው። የተለመደ የነጮች ጥያቄ በመሆኑ እንደወትሮዬ “ከአፍሪካ ነኝ” አልኳቸው። ብዙዎቹ እያንዳንዱ አገርን ለይተው የማያውቁ ስለሆነ ለወትሮው በቂ መልስ ነበር። “ከአፍሪካ ውስጥ ከየትኛው አገር ነህ?” ሲሉኝ በዋዛ እንደማንላቀቅ ተገነዘብሁ። ብዙዎቹ... Continue Reading →

Start a Blog at WordPress.com.

Up ↑