ለወቅታዊው የሃገሪቷ ቀውስ 7 የመፍትሄ ሃሳቦች

ለወቅታዊው የሃገሪቷ ቀውስ 7 የመፍትሄ ሃሳቦች

ስንገድለው ስንደበድበው . . . .
አምቦ ብቻ አይደለም ፥ በአምቦና በአዲስ መካከል ያለችው ቡራዩም የተቃውሞ አውድማ ሆናለች። ሱሉልታ፣ ሆለታ፣ ሰበታም አልጸዱም። አዲስ አበባ አፍንጫ ላይ ያሉትን አገዛዝ ማረጋጋት ካልቻለ፣ እንደ ዶዶላ፣ ባኮ፣ ነጆ፣ ቆቦ . . . . ያሉትን እንዴት ነው የሚያረጋጋው? በጉልበት፣ በኃይል ይሄን ኣይነት እኔ በእደሜዬ አይቼ የማላውቀውን ተቃውሞ ማስቆም የሚቻል አይመስለኝም።

የወያኔ ታጣቂዎች ተኩስ አቁመው በአስችኳይ ተቃውሞ ከሚሰማባቸው አካባቢዎች ለቀው እንዲወጡ እንጠይቃለን! እነርሱ ባሁኑ ጊዜ ለህዝቡ አለርጂክ ናቸው። የእነርሱ ብቅ ማለት ህዝቡን የበለጠ ያስቆጣል።
አሁን 11ኛው ሰዓት ላይ እንገኛለን። በኦሮሚያና በጎንደር የተነሣው ተቃውሞ የአዲስ አበባ ህዝብ ወይንም የጎጃም ወሎ የመሳሰሉት ከተቀላቀሉት ሁሉም ነገር አበቃ ማለት ነው። ያኔ ግን አያድርስ . . . . .

በሃገሪቷ ነገሮች ከቁጥጥር እየወጡ ይገኛሉ። ዋና ዋና መንገዶች እየተዘጉ ነው። የወያኔ ሹመኞች ከየከተሞች ሥልጣን እየተነሱ በህዝቡ እጅ እየገባ ነው። የአካባቢው ፖሊስ መቆጣጠር ሲያቅተው የፌዴራል ፖሊስ ይተካል። የፌዴራል ፖሊስ መቆጣጠር ሲያቅተው መከላከያ ሰራዊት (ልዩ ኃይል) ይሾማል።

ዳሩ ግና ሁሉም የደህንነት ኃይሎች ቀውሱን መቆጣጠር አልቻሉም። ስለዚህም የዚህ ሁሉ ቀውስ መውጫ መንገድ የፖለቲካ መፍትሄ መስጠት ነው።  ኃይልን በመጠቀም ተቃውሞን ለመበተንና ልዩነትን ለማጥፋት መሞከር ትርፉ ግጭትን ማባባስ እና ተቃዋሚዎቹን ወደ 4 ኪሎ መምራት ነው።

የመፍትሄ ሃሳቦች

1. ተጨማሪ ግጭትና የደም መፋሰስ ይበቃናል ስለዚህ ተቃውሞ ካለባቸው አካባቢዎች እና ከተማዎች ወታደሮችን ማስወጣትና የተኩስ አቁም ማወጅ።

2. ከእውነተኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች (መድረክ፣ ሰማያዊ፣ መኢአድ) ጋር የሽግግር መንግስት እንደሚቋቋም ማወጅ።

3. የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እንዲሁም የሱዳን ድንበር የማካለል ዕቅድ ማቆም

4. ሁሉንም የህሊና እስረኞች መፍታት። ሁሉንም። ካልሆነ ግን ህዝቡ ራሱ በመጨረሻ ነጻ ያወጣቸዋል።

5. የዲሞክራሲ ተቋማትን ሚዲያ፣ ምርጫ ቦርድ፣ መከላከያ፣ ፖሊስ፣ ፍርድ ቤት . . .  የሚያሻሽል ገለልተኝ ኮሚሽን መመስረት።

5. የአሁኑን ህገ መንግስት እና የፌዴራል መዋቅር የሚያጠናና ለህዝብ ውይይት የሚሆን ዕቅድ የሚያዘጋጅ ገለልተኛ ኮሚሽን ማቋቋም።

6. በሁነቶቹ ጀርባ እጃቸው እንዳለ የሚታመኑትን እንደ የደኅንነት አለቃው ጌታቸው አሰፋ፣ የመከላከያ አለቃ ሳሞራ የኑስ ያሉትን ዋና ዋና ሹመኞችን ማንሣት። እነዚህ ሰዎች በኃላፊነት እያሉ መንግስቱን ልናምነው አይቻለንም።

ሸገርም ከተቃወሞ አውድማነት የምትቀር አትመስልም። ዘገባዎች አለመረጋጋቱ ወደ አዲሰ አበባ ሊመጣ እንደሚችል ይገልጻሉ።ሀገራችን ወደ ሥርዓት አልበኝነት እንድትገባ አንፍቀድ!!

Leave a comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

Start a Blog at WordPress.com.

Up ↑