የግንቦት ፍሬዎች ሁለት To Read in PDF ዘመነ ግንቦታውያን ከሰጡን ፍሬዎች መቅመስ ጀምረናል። የጎልማሳው ትውልድና የተተኪው ትርክት እንደቀጠለ ነው። ከፍሬዎቹ አንዱ በሆነው የዜግነት ክብር ላይ ዛሬ እንቆያለን። ከዚህ ቀደም በዚህ ርእስ ላይ ጽፌ ነበር። ይሄኛው ጽሑፍ ዝርዝር ዜናሁ ነው። ሰው በመሆን ጸጋና በጥቅሙ ደስታ አንድ ሆነን ተሰርተናል። በምንኖርበት ሥፍራ ባስቀመጥናቸውና በተቀመጡብን አለቃዎች ምክንያት ይህ የሰውነት... Continue Reading →
የግንቦት ፍሬዎች
የግንቦት ፍሬዎች የግንቦት ወር ተለይቶ የሚታወቀው ፀሓያማ ወር በመሆን ነበር። የመስከረምን ድርሻ ከነጠቀ በኋላ ግን ዝነኛና የማይረሳ አዚማም እና ተስፋ ፈንጣቂ ወር በመሆን ተገልጧል። አሁን ግን ብዙን ነገር ተቀያይሯል ከሩብ ምዕት ዓመት በኋላ የአንድ ትውልድ ዘመን ጎልምሶ ሌላኛው ተተኪ ትውልድ እየበቀለ ይገኛል። ለእኒህ ትውልዶች ታሪካቸው ግንቦትን በወራት ሁሉ ላይ ነግሦ ሲንገዋለል ከትቦታል። የብር ኢዮቤልዩ (ሃያ... Continue Reading →
ኩሩ ኢትዮጵያዊ ለመሆን አንድ ተጨማሪ ምክንያት -አድዋ ዜና መዋዕል
ኩሩ ኢትዮጵያዊ ለመሆን አንድ ተጨማሪ ምክንያት -አድዋ ዜና መዋዕል <<የዛሬ ሳምንት አድርገው!! በዚህ ላንተ የሚደነግጥ ሰው የለም። ሂድ የፎከርክበትን አሁኑኑ አድርገው። እኛም የመጣውን እንመልሰዋለን። እግሩን ለጠጠር፣ ደረቱን ለጦር ሰጥቶ አገሩን የማያድን ሰው የሌለ እንዳይመስልህ። ደሙን አፍስሶ ለአገር መሞት ጌጥ ነው እንጂ ሞት አይባልም። አሁኑኑ ሂድ አይምሽብህ፣ የፈከርክበትን ባሻህ ጊዜ ታደርገዋለህ። እኝም እዚያ እንጠብቅሃለን። እኔ ሴት ... Continue Reading →
ኩሩ ኢትዮጵያዊ ለመሆን አንድ ተጨማሪ ምክንያት -አድዋ ሁለት
ኩሩ ኢትዮጵያዊ ለመሆን አንድ ተጨማሪ ምክንያት -አድዋ ሁለት ኩሩ ኢትዮጵያዊ ለመሆን አንድ ተጨማሪ ምክንያት ያገኘንበት ታሪክ የየካቲት ሃያ ሦስቱ የአድዋ ድል ቀጣይ ክፍል ቀጥሏል። TO READ IN PDF የአድዋ ጦርነት በኢትዮጵያውያን አኩሪ ድል ቢጠናቀቅም ዳግማዊ ምኒልክ የጦር ኃይሉ ድካምና ለመሰጠት (ለመዋጋት) ያለው አቅም መመናመንን ተከትሎ ጣሊያንን ከባህር አሻግሮ አልገፋውም። በመቶዎች የሚቆጠሩ የጣሊያን የጦር ምርኮኞች ወደ... Continue Reading →
የኛ ሠፈር ፍርድ
የኛ ሠፈር ፍርድ እኛ ሠፈር ነው፡፡ አንዲት ሴትዮ በእኩለ ሌሊት እሪታዋን አቀለጠቺው፡፡ እኛም እየተንጋጋን ከቤታችን ወጣን፡፡ ሠፈርተኛው፣ የአካባቢ ጸጥታ አስከባሪዎች፣ መንገደኛው፣ የቀበሌ ሹሙ፣ ውሾቹ እንኳን ሳይቀሩ የተጮኸበት ቤት ጋ ተሰበሰቡ፡፡ ጎረምሶቹ የቤቱን በር ሰብረው ሲገቡ ባሏ ሚስቱን ውኃ ውኃ በሚያሰኝ ዱላ ይደበድባል፡፡ ጎረምሶቹ ዱላውን ነጥቀው እርሷን ከቤት አወጧት፡፡ ልብሷ ተቀዳዷል፤ የተረፈውም በደም አበላ ተጠምቋል፡፡ ከጸጥታ... Continue Reading →
የኢትዮጵያ ርዕዮት ተናገረች
የኢትዮጵያ ርዕዮት ተናገረች July 14, 2015 ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ አይበገሬዋ ጀግናዋ ርዕዮት! በንጹሀን ዜጎች ላይ ስቃይን በመፈጸም ከሚታወቀውና ከአዲስ አበባ ከተማ እምብርት በስተደቡብ ምስራቅ ተንጣሎ ከሚገኘው እና በተለምዶ ቃሊቲ እየተባለ ከሚጠራው የመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት (የኢትዮጵያ “ሮቤን ደሴት” ማለትም ነልሶን ማንደላ የታሰሩበት) ባልተጠበቀ ጊዜ የተለቀቀችው ጀግናዋ ርዕዮት ዓለሙ ከማጎሪያው እስር ቤት... Continue Reading →
የመልካምነትና ክፋት ድልድይ
የመልካምነትና ክፋት ድልድይ “በጎን ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን ነው?” 1ኛ ጴጥ 3፥13 ረጅም ጊዜ የቆየ ጓደኝነት ነው ያለን፡፡ ዛሬ ሳገኛት በሐሴት ውስጥ ነበርኩ፡፡ በጨዋታችንም መሐል በአእምሮዬ ተደጋግሞ የሚመላለስውን ጥያቄ አነሣሁት፡፡ “ሰው ግን ለምንድነው እንዲህ ክፉ የሆነው?” ስል የጓደኛዬ አተያይ ሁልጊዜም ይማርከኝ ነበርና ነው ከእርሷ ጋ መጫወት መሻቴ፡፡ ግን እውነት ሰው ስለምን ነው እንዲህ ክፋት የተሞላው?... Continue Reading →
የሐዘን ዘመን-እምባችንን ለማን?
የሐዘን ዘመን-እምባችንን ለማን? ወቅቱ ለኢትዮጵያውያን እጅግ አሳፋሪና አሰቃቂ ዘመን ሁኗል፡፡ እምባችን እንደጎርፍ ቢወርድም ብሶታችንና ሐዘናችንን ጠርጎ መውሰድ አልተቻለውም፡፡ ይልቁን ብዙ ባነባን ቁጥር ብዙ ምናነባበት ይፈጠራል፡፡ እኛ ከሌሎች ሃገራት ዜጎች የተለየን የሰው ፍጡሮች አይደለንም፡፡ ኢትዮጵያዊነት ሰውነት ነው፡፡ የዓለም ዜጋዎች ነን፡፡ የአፍሪካ መንደርተኞች ነን፡፡ ኢትዮጵያ ደግሞ የትውልዳችን ወይም የመኖሪያችን ሥፍራ ነው፡፡ ለዚህ ስያሜ ከቀሩት የዓለም ፍጡራን በተለየ... Continue Reading →
ስለ እኔ አታልቅሱ
“ስለ እኔ አታልቅሱ” (ይህ “ኑ! እንዋቀስ”የሚለው ስር ነቀል የለውጥ ጥሪ ቀጥታ የሚያነጣጥረው በኢህአዴግ አባላት ላይ ብቻ ነው፤ አመራሩን በፍፁም አይመለከትም) ከተመስገን ደሳለኝ “ዋይ ዋይ ከሚሉና ሙሾ ከሚያወጡ ሴቶችና ከሕዝቡ እጅግ ብዙዎች ተከተሉት፡፡ ኢየሱስ ግን ወደ እነርሱ ዘወር ብሎ እንዲህ አለ፡- እናንተ የኢየሩሳሌም ልጆች ለእኔስ አታልቅሱልኝ፤ ዳሩ ግን፡- መካኖችና ያልወለዱ ማኀፀኖች፣ ያላጠቡ ጡቶችም... Continue Reading →
ኦሮማይ-በበአሉ ግርማ
በበአሉ ግርማ ከጎራው ዘልቄ እስኪ ልነጋገር ካለሰው ቢወዱት ምንያደርጋል ሃገር? የኔ ውብ ከተማ ህንጻ መች ሆነና የድንጋይ ክምር የኔ ውብ ከተማ መንገድ መች ሆነና የድንጋይ አጥር የኔ ውብ ከተማ የኔ ውብ አገር የሰው ልጅ ልብ ነው የሌለው ዳርቻ የሌለው ድንበር፡፡ ህንጻው ምን ቢረዝም ምን ቢጸዳ ቤቱ መንገዱ ቢሰፋ ቢንጣለል አስፋልቱ ሰው በሰው ካልሸተተ ምንድነው ውበቱ?... Continue Reading →