እድሜ ዘመን ቁጥር

እድሜ ዘመን ቁጥር

ህልውናዬ ጸድቆ እስትንፋስን ስ’ቸር

እኩል ዘመን ሰፈርን እድሜዬና ምድር

እሷ …….

የዓመት ትግሏን ጨርሳ በወቅት ስትከፈል

ከጽጌ ‘ቅፍ ገብታ ድካሟ ተረስቶ መንፈሷ ታድሷል

እድፍ ገላዋ ነጽቶ ባ’ዲስ ልብስ ሸብርቋል

ይኽን ትቆጥራለች…………. አንድ ሁለት እያለች፡፡

እኔ……….

ፍላጎቴ በዝቶ መልኬ ተቀይሯል

ሥጋዬ ጀግኖ ዓለሙ ጠቦኛል

እኔም እቆጥራለሁ…….. አንድ ሁለት እላለሁ

የእድሜዬን ወረት ባዶ እያስቀረሁ፡፡

ነፍሴ ግን ደህይታ  በረከቷ ጠፍቶ

ምጣቷን ስታስብ ስቃይዋ በርትቶ

ማልቀስን ይዛለች……. መቁጠር አቁማለች፡፡

ይኸው……….

አዲስ ዓመት ጠባ…….. ዘመንን ገለጠ

የሥጋዬ ቁመት ዘመን ተሻገረ በቁጥር አበጠ

ሕይወቴ ቱሩፋት ሠናይ-ምግባር ተርቦ ለትላንት ተሰጠ፡፡

ዛሬ……..

እድሜና ዘመንን……….. ቁጥር ሲገልጻቸው

ነፍስና ሥጋዬን………… ቁጥር ለያያቸው፡፡

 

ነሐሴ ፳፯፣፳፻፩ዓ.ም

አዲስ አበባ

Leave a comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

Start a Blog at WordPress.com.

Up ↑