ምስል አልባ ፊደላት

ምስል አልባ ፊደላት

     እይታው እንዲህ ነው…..

ቋሚው አዘንብሏል ውስጡ ተቦረትፎ

ማገሩም ተመዟል ግድጊዳው ተምሶ

የቀለም ድርቅ መቶት አፈር አፈር ሆኗል

ጣራው ጨቅይቶ ጽልመት ተላብሶ እይታን ተነፍጓል

ደጁ ‘ደርሻ ታርሶ ተኮትኩቷል ለቁሻሻ ተክል

በሩ.. መዝጊያነቱ ቀርቶ መከለያ ሆኗል

ለመዝጋ ቢታሰብ ከጩኸቱ፣ ከትግያ በላይ አቅሙ ይታጎላል

ቀንም ሆነ ማታ ጭለማ ተውጦ ዓመታት ተቆጥሯል፡፡

አዎ!

ጎረቤቱ ብዙ መንደሩ ሰፋ ይላል

በህንጻ ተሞልቶ በቀለም ተውቦ እይታዎች ሰልቧል

በየህንጻው ብርሃን በየቤቱ ድምጸት ህያውነት ዘርቷል

ያቺ ደሳሳ ጎጆ በመጸየፍ ተከባ ህይወቷ ተረስቷል

የዛ ልዩ ፍጡር እምቅ ኃይል ባለቤት ሰውነት ተሽሯል

ህይወት እስትንፋሷ ካ’ማረ ህንጻ’ጂ ከጎጆ ተሰዷል፡፡

እውነታው እንዲህ ነው…..

ሠላም ጽልመት ተላብሶ ብርሃን ተጸይፎ ባ’ርምሞ ተከቦ

ሳቅ ድምጽን ተቃርኖ ከልብ ተወዳጅቶ ለሆሳስ ደርቦ

ነጻነት ክብሩን እያበራ ጭለማውን ሲውጥ

ጤንነት ጓዙን ሸክፎ ዝምታን ሊዋሃድ

ደስታ አጎንብሶ ከዘመመ ጎጆ ገብቷል ሊስተናገድ!!

ያኔ ህብረ ዜማ እያዜሙ ህሊናን አቅንተው

ስብእናን አግዝፈው

በብቻነት ዓለም እርካታን ወለዱ በጭለማ ፈክተው፡፡

እርግጥ ነው!

እርግጥ ነው የጥርስ ሳቅ ሁሉ ደስታ አይኖረውም

ሁካታ ጨዋታ ደስታ በማመንጨት ከዝምታ አይበልትም

ቱባውም እርካታ በሥጋ ምቾት ብቻ ህይወትን አይዘራም

ለዚህ ነው…..

ፍጹም ነጻነት ከግዞት ተላቆ ካ’ጌጠ ቤት ጠፍቶ

ከደሳሳ ጎጆ ከጭለማው መሐል የታየው አብርቶ!!

ግንቦት ፬/፳፻ ዓ.ም

አዲስ አበባ

2 thoughts on “ምስል አልባ ፊደላት

Add yours

  1. wondima endemin aleh? ena tikur neger silemaliwod endehone alawikim manibeb alichalikum, ye mestafia seladaw nech hono tsuhufu betikur byhon des yilegnal! ke misigana gar!

Leave a comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

Start a Blog at WordPress.com.

Up ↑