ሠላም!
እንዴት ሰነበታችሁልኝ መቼም ምስጋናዬ እጅጉን የበዛ ነው፡፡ የጦማሬ ተከታታይ ናችሁና፡፡ በምታገኟቻ ጦማሮች ላይ ያላችሁንና የተሰማችሁን ብትጽፉልኝ ደስታዬ ወደር አልባ ይሆናል፡፡
ትንሽ ጠፍቻለሁና ከይቅርታ ጋር እንኳን ለበዓለ ልደት መዳረሻ አደረሳችሁ በማለት ይቺን ጀባ ብያለሁ፡፡

ፈኑ እዴከ
| “በ |
የትውልዳችን በዘመናት ሐረግ በዛ ልመናችን
ተስፋችን ቃልኪዳኑ ርቆ ባርነት ተሰጠን
ጽድቃችን ድካሙ ዋጋ’ቶ የመርገም ጨርቅ ሆነ
ኃጢአትን በውርስ ተቀባብለን ነፍሳችን ጣመነ
የባርነት እስራት ግዞቱ ይብቃ ይለፍ በ’ኛ ላይ
ፈኑ እዴከ እ’ማርያም የ’ኛን ስህተት ሳታይ!”
እያለ የዋጀው ዘመኑን ዋጋው ተቆጠረ
ሐዘኑ ዕንባው ታብሶ ተስፋውም ሰመረ
አርያም ተከፍቶ የኃጢያት ግድግዳ በክንዱ ፈረሰ
ምድር በምስራች በደስታ ተዋጠች ሠላምም ነገሠ
እጁን ምድር ሲልክ ባርነት ተገፎ ተስፋ ሕይወት ተዘራ
የጨለማው ዘመን አሮጌው ተሽሮ በልደቱ በራ፡፡
ሰማይና ምድር ሰውና መላእክት ኅብረትን አወጁ
ፍቅር ሠላም ነግሰው ይቅርታን ሰብከው የሰው ልጅን ዋጁ፡፡
በበረት የተኛው ፍቅር ሠላም እርሱ ይቅርታ ነው
ለሰው ያለው መውደድ ሰሀቦ እመንበሩ ከአእምሮ በላይ ነው!!
ታኅሳስ ፳፻፪ዓ.ም
አዲስ አበባ
Leave a comment