ሆሣዕና በአርያም! ሆ..ሣ.ዕና በአ…ር.ያም!
በአርያም በልዕልና ጸንቶ የሚኖር ከአርያም የተገኘ መድኃኒት ማለት ነው። እምሆሣዕናሁ (መድኃኒት ከመሆኑ የተነሣ)
- አርአየ ተአምረ ወመንክረ– ፍጹም ተአምራቱን ገለጸ
- አእምሮ ጠባይ ያልቀናላቸውን ሕፃናት አእምሮ ጠባይ ቀንቶላቸው፤ ንባበ አእምሮ ለሌላቸው አዕባን ንባብ አእምሮ ሰጥቶ እንዲያመሰግኑት አድርጓል። ግትነቱን ገልጦ።
- አርአየ ጸጋ ወኃይለ– ከሥልጣኑ ሳይለይ በጽርሐ አርያም በዘባነ ኪሩብ ባለ በምድር ልጅነትን ከሃሊነትን ገለጸ።
- ለኃጥአን አንብዓ ንስሐን፣ የበደሉትን ያከብራቸው ዘንድ፤ ከኃጢአታቸው ያነጻቸው ዘንድ፣ የሳቱትን በንስሐ ይመልሳቸው ዘንድ ለዕውራነ ሥጋ ዳግመኛ ብርሃን ሰጠ። እርሱም ካደረ የማይለይ ከተሰጠ የማይነሣ እውቀት የሚሆን ነው። ቅዳሴ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ምዕራፍ 2 ቁጥር 14-18 (ትርጓሜ)
ክብር ምሥጋና በጌታ ስም ለሚመጣው፣ ለመጣው!
ማነው ‘ሚያወጣኝ ከትልቅ ተራራ?
አሻግሬ ‘ዳይ ፍጻሜ-ትንቢትን ሲጣራ።
የንግስናሽ እድሜ ሰላምሽ ዛሬ ነው
መስቀል አዘጋጅተሽ ትቀበይው ምነው!
እንዳሉት ነብያት ፍጻሜው ተገኝቷል
በአህያ ተጭኖ ቅጠል ያስነጥፋል
ለመርገጡ ዋጋ አርብ ላይ ሊከፍል።
ማነው ‘ሚወስደኝ ከመልክአት ጠረፍ?
ቅኔ ‘ዳያመልጠኝ በ’ፃናት ሲዘረፍ።
የ’ባክህ አድነን አሁኑኑ ምጣ
ወረቡ ተቃኘ መቋሚያውን ይዞ ካህኑ ሲመራ
አህያዋ አዜመች ከድንጋይ ተባብራ።
ማነው ‘ሚያወጣኝ ከደስታ ሰገነት?
ትካዜን እንድገድፍ ቁልቁል እያየኋት
ለ’ርሷስ የምን ልቅሶ በሀዘን መወጋት
ደስታዋ ይብዛ ለሕመምተኞች ቤት
በአህያ ተጭኖ መድኃኒት መጣላት!!
ግንቦት ፳፻፭

Leave a comment