ከ https://soundcloud.com/atuadub/enya ላይ የተደመጠ
በትግስት ማሞ
እኛ
ን’ጎርሰው ሳይኖረን እኖረው ሳይኖረን
ባዶ ተስፋ መሐል መጪውን ሞሽረን
የሰጡንን ቀምሰን ባሉን አሜን ብለን
ባንድዬ ቸርነት አይችሉትን ችለን
ተገፍቶ የማያልቅ ጉድ ዘመን ተሻግረን
ይኸው ዛሬም አለን
ህልማችን መሐል ላይ ስደት ተስሎበት
በልባችን ሙሉ ራስ መውደድ በቅሎበት
ኑሯችን ጫፉ ላይ ፍርሃት ቋጥረንበት
እምኝ ብርቃችን ነው
መዘመን ከሆነ አዎን ዘምነናል ፈሪ ለ’ናቱ ነው መፍራት ይሻለናል
መሰልጠን ከሆነም አዎ ሰልጥነናል ሃገር ምንያደርጋል
ትውልድ ምናባቱ እኔነት መርጠናል
አዎን ሰልጥነናል አዎን ሰይጥነናል
የሰው ሰርግ አድማቂ አጃቢ ሆነናል
ሕይወቱን የጠላ አንድ ሞኝ ምስኪን ሰው ደፋር እስኪመጣ
ተስፋችንን በፍራት ትውልዱን በፍዘት በግፍ የምንቀጣ
ዛሬ በልቶ ማደር የህሊናችንን ሚዛኑን ያሳተን
ተመሳስሎ ኑሮ አጨብጭቦ ሹመት በባርነት ስለት የሚበላልተን የሚዶላልተን
የምንኖር መሳይ የሆነልን መሳይ የምንቆም ሞተን
እንደዚያ ነን እኛ
አሉላ ሞኝ ነው ደረቱን መስጠቱ ቴድሮስ የዋህ ነው ባሩድ መጠጣቱ
ገብርዬም ሞኝነው ድፍረት ማነገቱ ከመፍራት ነገ አለ ዘራፍ ምናባቱ
በሚል ስልጣኔ በሚል ስይጣኔ ዝምነትን ታቅፈን
የጀግኖቹን ኑረት መንፈሱን አራክሰን ጉድ ይዘን ጉድ ፈርተን
አለ ብለን እያልን ሁለት ጊዜ ሞተን ሲስቡን ተጎተን ሲለቁን ተደፍተን
ባንዲት ድፍረት እጦት ዘላለሙን ታመን
ቆመን እየሄድን በስጋት መንምነን ይኸው ዛሬም አለን
ቴድሮስ ሞኝነው ባሩድ መጠጣቱ
ገብርዬም የዋህ ነው ለመትረየስ እሳት ደረቱን መስጠቱ
ተወን ብለው ሲሉት ዝምበል ብለው ሲሉት እምቢየው ማለቱ
ድፍረት ምን ይሰራል ሃገር ምን ያደርጋል መሞት ምን ያመጣል እምቢኝ የ’ታባቱ
በሚል ስልጣኔ በሚል ስይጣኔ እየደነቆርን
ፍቅርን ስንቀማ ፍትህ ስንቀማ ይኸው ለዘመናት እንዳቀረቀርን
ዝም አልን
ልባችንን እንዲህ በሽብር ወጋግቶ ማነው የበለተን
ሞታችንን የሚያይ ፍርሃት የሚወርስ ትውልድን ጎልተን
ቁጭት እየበላን ንዴት እየጠጣን እምቢኝ እንልበት በቃን እንልበት
እውነት መተንፈሻ አንዲት ቃል እያጣን
በምን ይሆን ስጋት በምን ይሉን ፍራት እየተቀጣጣን ለማናቀው ነገ ዛሬ’ችንን አጣን
አለማወቋ ነው ሞኝ ናት ጣይቱ
እኛ ካልኖርንብት ሃገር ም’ናባቱ
በሚል ስልጣኔ ፍርሃት እናሽሞንሙን ተረት እንተርት እስኪ እንቀኝ ቅኔ
ባንዲት ደሃ ሃገር ባነዲት ት..ልቅ ሃገር
የትላንቱ መንፈስ የሚያስጋልባቸው ዝንመት ስልጣኔ ብልጠት ያልገባቸው
ለሰው ግራ የሆኑ ሰው የማይገባቸው
አንድ ሰው ነበሩ እድሜ ‘ጠገባቸው
በየመንገዱ ላይ በቀን በሌሊቱ ይለፈልፋሉ
ሰው ይጠይቃሉ መልስ ይጠብቃሉ
“ነጻነት ያያችሁ ፍትህን ያያችሁ………” ይላሉ
ሰዉ ይሸበራል ምነካዎት ዛሬ ምነው ዝም ቢሉ
“ወጣቱን ያያችሁ ትውልዱን ያያችሁ” ሰው ይጠይቃሉ መልስ ይጠብቃሉ
ሰዉ ይሸበራል ጉድ ፈላብን ዛሬ ኧረ ዝም በሉ
“ሌላም ጥያቄ አለኝ መልሱን እባካችሁ ኢትዮጵያን ያያችሁ
የጥንቱን አንድነት ፍቅሯን ያገኛችሁ ሃገር ጠፍቶብኛል ሃገሬን ያያችሁ”
ሃገር ብሎ ነገር ፍቅር ብሎ ወሬ
አንድነት ብሎ ቃል አልገባን እኛ ይለፈን ለዛሬ
እንደውም ጭራሹን ምንም አልገባንም ምንም አላየንም ተዉን እባካችሁ
እርሶ’ስ ብዙ አይተዋል እኛ መች ኖርንና ታስፈጁናላችሁ
ተዉን እባካችሁ ተዉን!!


Leave a comment