ምን ዓይነት ለውጥ?
የብዙህ ሰው ሐሳብ ይመስለኛል-በውስጣችን የነበረው። ባ’ንድ ወቅት ካ’ንድ ወንድሜ ጋር ኢትዮጵያ አሁን ስላላት መልክ (ምን እንደምትመስል) ለመሳል ስንሞክር ነበር- በመስመር ሳይሆን በቃላት ጨዋታ። እርግጥ ቀላል ነው ማንኛውም ሰው ኢትዮጵያ እንዴት ሆና ልታያት ትፈልጋለህ ተብሎ ቢጠየቅ
“በቴክኖሎጂና ፈጠራ የበለጸገች”
“ከድህነት የተላቀቀች”
“ዲሞክራሳዊ አስተዳደርና ሥርዓት የተሟሉላት..” የመሳሰሉትን መመለሱ አይቀርም። እኛም በጥቅሉ እንዲሁ ብለን ነበር። እንደነዚህ ዓይነት መልሶች አንዳች አሁን ያልሆኑ ወይም ያልተሟሉ እንዲለወጡ፣ እንዲሻሻሉ አሊያም እንዲቀየሩ የሚፈለጉ ጉዳዮች እንዳሉ አመላካች ናቸው። ለውጥ ሲባል በተለይ በድህነት ብቻ ሳይሆን በብዙ ነገር ራሷን የረሳች ወይም የተወችና ከሌሎች ወደኋላ የቀረች ሃገር ያለን እኛ ብዙ ዓይነት ለውጦች እንደሚያስፈልጉን ይታመናል። ጥያቄው ግን ምን ዓይነት ለውጥ? ምን ዓይነት መሻሻል? የሚለውን ማመላከቱ ላይ ይሆናል።
ይሄን ለመመለስ ባደረግነው ሙከራም ነው አሁን ያለችዋ ኢትዮጵያ ምን ትመስላለች የሚለውን መልኳን ለመሳል የሞከርነው- ባንጨርሰውም ቅሉ። እንደው እናንተስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይሰማችኋል? ማኅ በራዊ ወግ (ጨዋታ) ብናደርገው የሚበጅ ይመስለኛል። የሚሰማችሁን ጻፉልን። ለውጥ ያስፈልገናል? ምን ዓይነት ለውጥ ያስፈልገናል? ይሄን የምታነቡ ምላሽ ሳትሰጡ ባትወጡ ደስታዬ ወደር ባጣ! ሠናይ ሳምንት ይሁንልን።

በመሠታዊ ደረጃ የፖለቲካዊ ለውጥ ያስፈልጋታል! የለውጦቹዋ መሰረት የሚሆነው ግን የሕዝቡ ንቃተ ህሊና ላይ ለውጥ ለማምጣት ከተሰራ ነው።
በመሠታዊ ደረጃ የፖለቲካዊ ለውጥ ያስፈልጋታል! የለውጦቹዋ መሰረት የሚሆነው ግን የሕዝቡ ንቃተ ህሊና ላይ ለውጥ ለማምጣት ከተሰራ ነው።
there are so many things need to be change. sply, political and economical change are the most. for all changes political point of view alternation would be the roots.