ኩሩ ኢትዮጵያዊ ለመሆን አንድ ተጨማሪ ምክንያት -አድዋ

ኩሩ ኢትዮጵያዊ ለመሆን አንድ ተጨማሪ ምክንያት –አድዋ

To read in PDF

የካቲት ፳፫ ቀን ፲፰፻፹፰ ዓ.ም የ፻፳ ዓመት ታሪክ መዘከሪያ- የአድዋ ጦርነት። ወሳኙ የአድዋ ድል ዓለም ላይ ያሉ ጥቁር ህዝቦች ሁሉ የሚያወሩለት ተረክ ነው። አስደናቂ ድል ወይም አሳፋሪ ሽንፈት ከተወለደባቸው ቦታዎች የበለጠ ጥቂት ቦታዎች ጠንካራ ትዝታ ማስታወስ ይችላሉ።

ናፖሊዮን ቦናፓርት በ 1805 እ.ኤ.አ በኦስተርሊዝ (የአሁኗ ቼክ ሪፐብሊክ) ጦርነት የተባበሩተነ የአውሮፓ ነገሥታት ጦር በአሳማኝ ሁኔታ በማሸነፍ ከፍተኛ ዝና ያስገኘለትን ስኬት ተጎናጽፏል። ጥቂት ሽንፈቶችም ቢሆኑ ተሸናፊው ናፖሊዮን  (ከዛ በኋላ ንጉሥ) ተብለው ተመዝግበውበታል። ከ10 ዓመት በኋላ በ1815 እ.ኤ.አ በዋተርሎ (የአሁኗ ቤልጄም፣ ብራሰልስ አቅራቢያ) ጦርነት ንጉሡ ወታደሮቹ መሸነፋቸውን ሲረዳ “መሸሽ የሚችል ያምልጥ” በማለት ካስነገረ በኋላ በፈረስ ጀርባ ሁኖ ከጦርነት ሚዳው ሸሽቷል።

Minilk

አቧራማዋ የትግራይ ትንሽ መንደር የሆነችው አድዋ በዓለም ካርታ ላይ ልትሰፍር የበቃችው እንደ ኦስተርሊዙ ጦረኛ ናፖሊዮን ሳይሆን አስደናቂ በሆነ የጦር ስልት በአሳማኝ ሁኔታ የጣሊያንን ጦር ድል ባደረገው፥ ኃያልና ጀግና በሆነው በንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ነው። ስለዚህም በዚያች አንድ የአድዋ ድል ምክንያት ቦታ። ታሪክ፣ አፈታሪክ እና የማይሸነፈው ኃያሉ ተረክ ተወለዱ። በሁሉም ቦታ ባሉ የጥቁር ሕዝቦች በየትውልዳቸው፥ በተለይም የኢትዮጵያ ሕዝቦች መሃል የሚታወስ እና የሚደነቅ ታላቅ ኩራት ሆነ። የአሁኖቹ የጥቁር ሕዝብ ትውልዶች በያሉበት እንዲህ ይላሉ፥ ትልቅ ለመሆን የሚፈጠር የዝቅተኛነት ስሜት ምክንያት በልባቸው ከሚንቦለቦለው ቅናትና በነጭነት ከሞላው ጥላቻ የሚመነጨው ጩኸት ሊረብሸን አይገባም “ቀናቱ እነዚያ ናቸው”።

ሕዝቡም መሸነፍን እንደሚጸየፍና እንደሚቃወም አፄ ኃይለ ሥላሴ ከማይጮኹ ጦርነት በኋላ ወደ እንግሊዝ በተሰደዱ ጊዜ ያልተገራ ፈረስ ጠቅል ብላችሁ ሄደ ገሠገሠ ባህር ገባላችሁ  ተብሎ የተነገረው ስንኝ ያስረዳናል። እንዲህ መባሉ ያልተገባ ሂስ ነው፣ ምክንያቱም የማይጨው ጦርነት ለተከታታይ ስድስት ወራት የተካሄደ እና በሁሉም መንገድ ጦርነቱ በንጉሠ ነገሥቱ የተመራ ነበር በተጨማሪም ጣሊያን በዚህ ወቅት በምኒልክ ዘመን ከነበሩበት ከቆዩት የኢትዮጵያ የጦር መሣሪያዎች በብዙ የላቀና ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች ታጥቀው ነበር። ይልቁን የንጉሠ ነገሥቱን በጄኔቫ በሃገራት ህብረት (League of Nations) ላይ በጀግንነት የቆሙትና  “ዛሬ እኛ ነን፥ ነገ ግን እናንተ ልትሆኑ ትችላላችሁ” ያሰሙትን ትንቢታዊ ምልከታቸውን ማስታወስ ይገባናል። የሆነው ልክ እሳቸው እንዳሉት ነውና።

ምኒልክ በ ፲፰፻፸፮ ዓ.ም የተወለደ ሲሆን ከ፲፰፻፹፩ ዓ.ም እሰከ ፲፱፻፭ ዓ.ም ድረስ ንጉሠ ነገሥት ሁኗል። እርሱ ከካርቴጁ (አሁን በዘመናዊቷ ቱኒዚያ የሚገኝ ቦታ) ሃኒባል (247-183 B.C) ወዲህ በአፍሪካ የታየ ታላቁ የወታደራዊ ኃይል አዛዥ ነበር። የካርቴጂያው የጦር አዛዥ በዝሆኖች ወደ አልፕ ተራራ በመሄድ ሮማውያንን አሸንፎ ወደ አፍሪካ ተመልሶ እስኪጠራ ለ 15 ዓመታት ገዝቶ የኖረ ነው። ምኒልክ ወደ አድዋ በ 52 ዓመታቸው ሲዘምቱ ከሃኒባል አስር አመት ይበልጡ ነበር። ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆኑ የቀረውም ዓለም አድዋን ያስተሳሰረው ከምኒልክ ጋር እንጂ ከጊዜ ነዋሪዎች ጋር አልነበረም። ታሪክ እንደዚህ ነው የተፈጠረው፥ ምንም ያህል የኋላ ታሪክ ቢቸረቸር ወይም እንዳዲስ ታሪክን ለመጻፍ ቢሞከር ፈጽሞ ሊቀይረው አይቻልም። ከሌሎቹ አያሌ የሥራዎቹ ውጤቶች ጎን ምኒልክን ታላቅ ያደረገው በከፍታ የሚታየው የአድዋ ድል ውጤቱ ነው። ስለሆነም የቦታው ስም ለዘላለሙ (ለምንጊዜውም) ከእርሱ ጋር ተሳስሮ ይኖራል። እርሱ የወታደሮች ወታደር፣ በተፈጥሮው ጀግና፣ ፍርሃት አልባ እና የአንበሳ ልብ የያዘ ነበር። እንዲሁም ብርቱ የውጊያ መሪ እና የወታደራዊ መለኛ ነበር። የወታደሮቹን ፍጹም መሰጠትንና ታማኝነትን መቀስቀስ የሚችል የተለየ የጦር መሪ ነበር። ይህንንም ሰርቶ ያሳየ ነበር፥ መቶዎች ኪሎ ሜትሮችን ከአዲስ አበባ ወደ አድዋ ያደረገው ጉዞ የጀግኖች ታሪክ ትንሽ ክፍል እንደማለት ነበር። ወታደሮቹ በእግራቸው የተጓዙ ሲሆን የእነሱ ትጥቅም የተጓጓዘው በእንሰሳት (እንደ አህያ፣ ፈረስ፣ በቅሎ. .) ጀርባ ተጭኖ ነበር። የእንስሳቱ መኖ ሊዘጋጅና ሊጠበቅ ይገባዋል፣ ከፊት አስቀድሞ የውኃ ጉድጓዶች ሊለዩ ይገባል፣ እንዲሁም የወታደሩ ምግብ የማያልቅ አቅርቦት ሊኖረው ይገባል።

ምኒልክ ይመራ የነበረው ጦር ህብረብሔራዊ ጦር ነበር። በአብዛኛው ተመሳሳይ ቋንቋ የማይናገር ሁኖ ከሁሉም በላይ ሁሉን በሚያካተተው ኢትዮጵያዊ መለያ ላይ ባላቸው ከፈ ያለ ጽኑ እምነት በጋራ የተሳሰሩ ነበሩ። እንዲሁም ምኒልክ ከእግዚአብሔር የተሾመ ነው በሚለው ፍጹም ልበ ሙሉነታቸው ያላቸውን ጠቅላላ ፍቅርና መሰጠት ለእርሱ የሸለሙ ነበሩ። የምኒልክን እጅግ ሰፊ ጦር ሲንቀሳቀስ መመልከት ተአምራዊ የሆነ የከተማ መቆርቆርና ማታውኑ መፍረስን ምስክር የመሆን ያህል ነው ይህ ጀብዱ (ከፍተኛ ሙያ) አሁን’ኳ ለማሰብ የማይቻል ነው። ጉዞአቸው ታላቀ ጠመዝማዛ ወንዝ በርቀት ሲንቀሳቀስ እንደማየት ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ በጀርባቸው የተሸከሙ እንስሳት አሉ፥ እንደ አህያና ጠንካራ በቅሎ ያሉ ምግብና መጠጥ፣ ድንኳን እና የሚነድ እንጨት ተሸክመዋል። ለጦር አዛዦችና መሪዎች ደግሞ የሚሆኑ ፈረሶችና በቅሎዎች አሉ። ምኒልክ ሠላሳ ኃይለኛ ፈረሶችና በቅሎዎች አሉት። እነዚህም ለግሉ ለመጠቀም የተዘጋጁ ናቸው። ከአንድ ከደከመ ፈረስ ወይም በቅሎ ወደ ሌላኛው አዲስ እርምጃው ሳይገታ የሸጋገር ነበር።

ሌላው ጦር የሚመራው በባለቤቱ በእቴጌ ጣይቱ እና አነስተኛ ጦር የወደፊቷ ንግሥት፣ በወጣቷና ጉጉዋ ልጁ ዘውዲቱ ነበር። እሷም በራሷ ጎን የጦርነቱ ጀግኒት ነበረች። ስለ እቴጌ ጣይቱ ብዙ የተነገረ ቢሆነም በጦርነቱ ወቅት ከእንጀራናቷ እግር በግር ትከተል ስለነበረችው ወ/ሮ ዘውዲቱ ምንም አልተነገረም ማለት ይቻላል። ንጉሠ ነገሥቱን የኃይለ ሥላሴን ለማሞገስ ሲባል የእርሷ ንግሥና መጋረዱ የሚያሳዝን ነው። የልጅ ኢያሲም እንደዚያው ያረፈበት ቦታ እንኳ አይታወቅም። በወቅቱ እንዲህ ተብሏል

በ ኢያሱ ዳቦ ነው ትራሱ

በዘውዲቱ ተደፋ ሌማቱ

በተፈሪ ጠፋ ፍርፋሪ

የቅርብ ጊዜ ታሪክ ጸሐፊዎችም ቢሆኑ ለንግሥት ዘውዲቱ ዘመን ትንሽ ማውሳትን ቀጥለዋል። ኢትዮጵያ ወደ ሃገራት ማህበር (League of Nations) በእርሷ ዘመን እንደገባችና በራስ ተፈሪ ኢትዮጵያን በማዘመን ውስጥ ዋና አጋዥ መሆኗን መጥቀስ በቂ ነው። ከሁሉስ በፊት የእርሱ ተከታዮች ሁሉ በተነሣሱበት እና የሁላቸውም ታላቁ አዘማሚ የነበረው የምኒልክ ልጅ ናት። የምኒልክ ጥበብ በጨለማው ቀናቶች በዘመነ መሳፍንት ጠፍቶ የነበረውን ህብርብሔራዊ ጥንታዊ እምነተ አስተዳደር (polity) እንዲያንሰራራ የማድረግ ችሎታው ነው። አፄ ቴዎድሮስ የምኒልክ አሰልጣኝና አሳሪ የነበረ ሞክሮ ነበር ግን አልተሳካለትም። አፄ ዮሐንስ በከፊል ፍለጋውን ሞክሯል። ምኒልክ መሪዎችን የሚመርጠው በዘር ሃረግ ወይም በጎሳው ምንጭ ሳይሆን በችሎታና ባላቸው የጠባይ ብቃት ነው። ምኒልክ የሸዋ አማራና ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ነበረ። ከሙስሊምም ሆነ ከአማራ ውጪ ያሉ መሪዎችን ያምንና ይሾም ነበር። ምኒልክ የተወለደው ከውቢቷ አንጎሌላ መንደር ሲሆን የእርሱ ታላቁ ዝነኛ ኦሮሞ መሪ የሆነው ራስ ጎበና የተወለደው ዥው ካለ ገደል ጥቂት ማይልስ ርቆ ከሚገኘው ማንዲዳ ነው። ራስ ጎበና የምኒልክ አባት የንጉሥ ኃይለ መለኮት ታማኝ ተከታይ ነበረ። ምኒልክ ልዩ ችሎታን (ስጦታን) በመለየትና በመጠቀም የተለየ ችሎታ ነበረው። ወደ አድዋ ከዘመቱ የጦር መሪዎች መሃል ጥቂት ኃይል በወጣቱ ሀብተጊዮርጊስ ይመራ ነበር። እርሱም ከዘመናት በኋላ ፊታውራሪ እና የጦር አበጋዝ (minister) በመሆነ የምኒልክ የቅርብ ምስጢረኛ ሆኗል። እንዲሁም በምኒልክ ቤተ መንግስት ያደገው እና በኋላ ዝነኛ ጦረኛ የሆነው ደጃች ባልቻ እና ሌሎች ብዙ ከበዙ የኢትዮጵያ ክፍሎች ነበሩ። በርክሌይ ከአድዋ ጦርነት በኋላ ብዙም ሳይቆይ የጻፈው ምርጥ መጽሐፉ The Campaign of Adowa and the Rise of Menelik (1902) ላይ አቶ ሀብተጊዮርጊስን እና ወታደሮቹን ከንጉሠ ነገሥቱ ጦር በስተግራ ያሰማራበትን ይጦርነት ክልሎች ካርታ ይዟል።

ንጉሠ ነገሥቱ በጄኔራል ባራቴሪ የትእዛዝ እዝ ውስጥ ሰርስሮ የገባ ምስጢራዊ መረጃ አቀባይ ወይም ሰላይ ነበራቸው። ኣዋሎም የጣሊያን አዛዥ ሲሆን ዋጋ ያላቸው መረጃዎችን ለምኒልክ ያመጣ ነበር። ጣሊያኖች ወደ ኢትዮጵያ ተመሳሳይ መንገድ ተከትለው ከ አርባ ዓመት በኋላ ሲመጡ የኣዋሎም ቤተሰቦች ከአካባቢያቸው ተሰደው ነበር። ፋሲሽቶቹም በቀረው ቤተሰብ ላይ በገሃድ የበቀል እርምጃ ወስደውባቸዋል። በዚህ ጦርነት ወቅት ድላቸውን ለማንገስ ፋሲሽቶቹ ግዙፍ የሆነ የሞሶሎኒ ከተከሻ በላይ የሆነ ሃውልት በአድዋ ሊያውም በተሸነፉበት ስፍራ ላይ ገንብተው ነበር። ይህ ሃውልት ክማይልስ ርቀት ለመታየት የሚችል ነበር። ይህ ከተከሻ በላይ ሃውልት በዛን ወቅት በተጻፉ መጻህፍት ላይ ይታተም ነበር። (መጽሃፉን ባላስታውስም ስዕሉን አይቼ ነበር) ከአምስት አመት በኋላ የንግሊዝ የውጊያ ክፍል ወደ ፍርስራሽ እንደቀየረው ተነግሯል። እንግዲህ ታሪክ በጊዜ ውስጥ እንዲህ ነው የሚጓዘው።

ይቀጥላል ይቆየን

 

 

 

Leave a comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

Start a Blog at WordPress.com.

Up ↑