እግዚአብሔር አንድም ሦስትም እንዴት ይሆናል?

እግዚአብሔር አንድምሦስትም እንዴትይሆናል?

To Read in PDF

በቀደሙት ሁለት ክፍሎች ምስጢረ ሥላሴና ምስጢረ ሥጋዌን የሚያብራሩ ጽሑፎችን ማቅረባችን ይታወሳል። እግዚአብሔር ልጅ አለውን? በሚለው የመጀመሪያ ጽሑፍ እግዚአብሔር ልጅ እንዳለውና እርሱም እግዚአብሔር እንደሆነ አይተናል። በቀጣዩ እግዚአብሔር እንዴት ሰው ሊሆን ቻለ? በሚለው ጽሑፍም አምላክ ሰው ሊሆን ያበቁትን ምክንያቶችና እግዚአብሔር ሰው ሆነ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለመዳሰስ ሞክረናል። በዚህኛው ክፍል ደግሞ እግዚአብሔር ልጅ አለው እርሱም እግዚአብሔር የሆነ ካልን የምስጢረ ሥላሴን አስተምህሮ አንድነትና ሦስትነት ለማየት እንሞክራለን። ለዛሬውም ቤተ ፍቅር ዘአቢሲኒያ በተመሳሳይ ርእስ የተጻፈውን የግብጻዊውን አባ ታድሮስ ማላቲ ጽሑፍ ተርጉሞ አቅርቦልናል እንደሚከተለው ይቀርባል። እግዚአብሔር ልባችንን ይዳብሰው ይባርከን፥ አሜን።

ርስቲያን ያልሆኑቱ በተደጋጋሚ ይህን ይጠይቃሉ እግዚአብሔር አንድምሦስትም እንዴት ይሆናል? በማለት

  • በቅድስት ሥላሴ (በተለየ ሦስትነት) ማመን ያስፈልገናል?
  • በአንድ እግዚአብሔር የምናምን ከሆነ በቅድስት ሥላሴ (በተለየ ሦስትነት) ማመን ይገባናል?
  • የቅድስት ሥላሴ (የተለየ ሦስትነት) አስተምህሮ በአንድ አምላክ ከማመናችንን አስተምህሮ ጋር አይጋጭም?

ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ከመስጠታችን በፊት እግዚአብሔር አንድምሦስትም እንዴት ይሆናል? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ እንስጥ።

የአንድ አምላክ አስተምህሮ!

መጽሐፍ ቅዱስ በሁለቱም ኪዳናት ውስጥ በተለያዩ ሁኔታዎች የእግዚአብሔርን አንድ መሆን አስረግጦ ይናገራል። “ከሁሉ ፊተኛይቱ ትእዛዝ ማናቸይቱ ናት?” ተብሎ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲጠየቅ እንዲህ መልሷል “እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው” (ማር ፲፪፥ ፳፰፣ ፳፱) የእግዚአብሔርን አንድነት ስናስረግጥ የብዙ አምላክ አምልኮን (polytheism- የመለኮትን መባዛት) እና የጣዖት አምልኮን በመቃወም ነው። የእግዚአብሔርን መኖር የማይቀበለውን አስተምህሮም ሆነ የእግዚአብሔር ሁሉን አዋቂነት (omniscience) የሚጠራጠረውን ሃሳብ(agnosticism) ጭምር ባለመቀበል ነው።

ልዩ የሆነው የእግዚአብሔር አንድነት

እግዚአብሔር በሁሉም ነገር ልዩ ነው። ምንም እንኳ መጽሐፍ ቅዱስ “አንድ አምላክ” ብሎ ቢጠራውም ለሂሳብ ህግ ግን የተሰጠ ነው ማለት አይደለም ምክንያቱም እርሱ መጠን የሌለው [የማይወሰን] በመሆኑ (Infinite)። እግዚአብሔር አንድ ነው ነገር ግን በእርግጠኝነት ከአንድ ቁጥር የሚበልጥ ነው። እርሱ በሰማይም ሆነ በምድር ካለው ማናቸውም ነገር የሚበልጥ ነው።

በሌላ አነጋገር፥ “አንድ” ማለት ከብዙዎች መሐል ያለ ቁጥር ለማለት አይደልምና ለአጠቃቀማችንአዲስ ብያኔ መስጠትና መረዳትን መፍጠር ይኖርብናል።ልዩ፣ ነጠላ እና ሊገልጹት የሚያቅተውን የአምላክ ማንነት የሚገልጽ ነው። እግዚአብሔር ለቁጥር ሥርዓታችን እንዲሰጥ የተዘጋጀ ሊሆን አይችልም ይልቁን ከማንኛውም የሰውልጅ ሥርዓት በላይ የሆነ ነው እንጂ። የእስክንድሪያው ቅዱስ ቅሌሜንጦስ እንዲህ እንዳለ “እግዚአብሔር ከሁሉም አንድብ መሆኖች የላቀ ነው። ከአንድነት ከራሱም በላይ ነው።”

Holy Trinity-ቅድስት ሥላሴ

የእግዚአብሔር አንድነት አንድ ከሆነ አካል ላይ የተገለለ ነጠላ ራስወዳድ ማለት አይደለም። አንድነቱ ከመገለል አጥብቆ የራቀ የጠነከረ [የተጨበጠ] አንድነት ነው።[1]

ሦስት እንዴት አንድ ሊሆን ይችላል?

የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ እምነት [አስተምህሮ] የአብን የአባትነት ነገረ ሃሳብ የማስረዘም ጥረት ወይም የብዙ አማልክት አምልኮ ማሳያ አይደለም። ልጁ እንዲህ እንዳለ “እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ” (ዮሐ ፲፬፥ ፲) “እኔን ያየ አብን አይቶአል”(ዮሐ ፲፬፥ ፱) በቅድስት ሥላሴ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ አካል (Hypostasis)የሌሎቹን የሁለቱን ይሞላል፥ በውስጣቸውም ያለ ነው። ዳሩ ግን ከሌሎቹ በተወሰነ መልኩ [እንደምንም] የሚለይ ነው። ልክ የሰውን አእምሮ ከሰው ነፍስ መለየት እንደምንችለው። ምንም እንኳ እሱ [አእምሮ] ላይ የተጨመረ ወይም ከእሱ ላይ የሚለይ ባይሆንም ቅሉ። እዚህ ላይ አንድነት መጨ’መርማለት እንደሆነ አያመለክትም። በቅድስት ሥላሴ ማመናችን የእግዚአብሔርን አንድነት አይቃወምም [አያፈርሰውም]በአንድ መለኮታዊ ባህርይ (essences-ousia) የምናምን እንጂ በሦስት መለኮታዊ ባህርይ የምናምን አይደለንም። ይህን መለኮታዊ ምስጢር ለመረዳት መለኮታዊ ባህርይ ከዘላለም[2] ጀምሮ በመኖር ላይ ያለ ነው ማለት እንችላለን።ይህ ዘላለማዊ መኖር አሳቢ መኖር[3] ጭምር ነው። በሌላ አነጋገር፥ በራሱ መኖር (self existence) የተወለደ አእምሮ፣ ጥበብ ወይም ቃል[4] አለው ማለት ነው። ስለዚህም የመለኮታዊ አእምሮ ተፈጥሮ የአባቱን ያልሆነ የተለየ ባህርይ[5] የለውም። ዳሩ ግና ከአንድ ዓይነት የእግዚአብሔር ባህርይ ወጥቶ ተወለደ። መለኮታዊውን አካል (being) “አባት” እና ቃሉን “ልጅ” ብለን ስንጠራ ወልድ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ማረጋገጫ እየሰጠን ነው። ይህ ማለት ግን ሰለዚህ በሁለት አማልክት እናምናለን ወይም አብና ወልድ ሁለት ባህርያት ናቸው ማለት አይደለም። አትናጎራስ እንዳለው፥ ዘላለማዊው አምላክ ለዘላለም በውስጡ የኖረ አእምሮ (Logikos) አለው። መለኮታዊው ባህርይ[6] (አብ) ለዘላለም በሕይወት ያለ (የሚኖር) ነው። ሕይወቱ ከራሱ የተገኘ (የሰረጸ)ሲሆን ውጫዊ የእርሱ ባህርይ አይደለም። መኖሩ(existence) ከሕይወቱ የሚለይ ቢሆንም አንዳቸውም ከአንዳቸው የተለዩ (የተገነጠሉ) አይደሉም። አንዳቸውም የተለየ መለኮታዊ[7] ባህርይ የላቸውም ምክንያቱም ሕይወቱ ከዚህ ከመለኮታዊው መኖር ከራሱ ተገኝቷልና[8]

(የእስክንድሪያው ቅዱስ ዲዮናስዮስ)

በዘላለማዊ ባህርይ፣ ነጠላና ቀላል በሆነው አሳቢ ሕይወት ባለው ማንነት(አካል [9]ማመን አስፈላጊ ነው። ሦስቱ አካላት ለዘላለም የማይለያዩና አንዳቸውም ያለሌሎቹ ኖረው ፈጽሞ አያውቁም። እነርሱ ነበልባል ኖሮት በተመሳሳይ ሰዓት ብርሃንና ሙቀትን እንደሚረጨው እሳት ናቸው። በመሆኑም የእግዚአብሔር አንድነት ወደ ሦስትነት የሚከፋፈል አይደለም። ይልቁን ሦስቱም የሥላሴ አካላት የእያንዳንዳቸውን ማንነት ሳያጡ ይዋሃዳሉ እንጂ።

ቅድስት ሥላሴና ዓይነታችው

በክርስትና እምነት ውስጥ ምስጢረ ሥላሴዋነኛ የዶገማ አስተምህሮ ነው። በሰማይ እና በምድር ያለ ሕይወታችንን የሚነካ፣ ስውር፣ የማይገነዘቡት ምስጢር ነው። የቤተ ክርስቲያን አባቶች ከፍተኛ ጥረት በማደረግ ይህንን ምስጢር ለማስረዳት ሞክረዋል። መለኮትን ለመግለጽ የሰው ቋንቋ ደካም ነው እንዲሁም ተፈጥሮ በሞላው የነጠላ [አንድ] ባህርይን[10] ከሦስት የተለያዩ አካላት ጋር መኖራቸውን የሚያስረዳ እውነተኛ ምሳሌ ያጥረዋል።

ይህን ምስጢር ለመረዳት በራሱ መኖር የግድ አስፈላጊ የሆነ ብቸኛ አካል[11] እግዚአብሔር ብቻ ነው እንል ይሆናል። ሁለት መደብ የሆኑ መለያ ባህርያትና አእምሮአዊ ትእዛዛት ያሉትን ይህን በራሱ መኖርን ነው መለኮታዊ ባህርይ ያልነው።የተወሰኑት መለያ ባህርያት የግልና የእግዚአብሔርን የራሱን ማንነት[12] የሚመለከቱ ሲሆኑ ሌሎቹ መለያ ባህርያት ከተፈጥሮ [ከፈጠራቸው] ጋር ያለውን ግንኙነት የሚመለከቱ ናቸው። ሦስቱ የግሉ መለያዎች የሆኑት መኖር (መሆን)[13]፣ ምክንያት (Logos) እና ሕይወት ናቸው። እነዚህ ሦስቱ መለያ ባህርያት ከእሱ ውጭ እንደተገኙ ሁነው በእግዚአብሔር ባህርይ (essences) ላይ የሚጨመሩ አይደሉም ይልቁን ለዘላለም ሳይነጣጠሉ ከራሱ መለኮታዊ ባህርይ ውስጥ የተገኙ ናቸው። መለኮታዊ መሠረቱ[14] (substance) ያለ ምክንያትና ከሕይወት ውጪ የኖረበት ምንም ዓይነት ጊዜ የለም። አብ መነሻ (መኖር) ሲሆን ወልድ ተመሳሳይ መለያ (ቃል መሆን[15]) ባህርይ ያለው፣ መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ሕይወት ነው።

እዚህ ላይ ይሄን ማጤን ጠቃሚ ነው። ሦስቱ አካላት (Hypostasis) የሚለያዩ አይደሉም ዳሩ ግን ተመሳሳይ ባህርይ አላቸው፣ ሥራቸውም የማይነጣጠል ነው።

የተፈጥሮ ምሳሌ

በመጀመሪያ ደረጃ የሚከተሉት ማናቸውም ምሳሌዎች በቀረበና በተወሰነ መልኩ ምስጢሩን ለማብራራትና ጥቂት የብርሃን ዳስ ለመሆን ይችላሉ። እነዚህ ምሳሌዎች የምስጢሩን አንደኛውን ሁኔታ ወይም ሌላኛውን ብቻ እንደሚያብራሩ ግንዛቤ መውሰድ ይገባል።

ሁለተኛው፥ ይህን ምስጢር ለመርዳት ከእግዚአብሔር ጋር አንድነት እንዲኖረን የሚያደርግ የመለኮታዊ ጸጋ ያሰፈልገናል። ይኸውም በመንፈስ ቅዱስ ውስጥ በልጁ ከአብ ጋር የሚኖረን ኅብረት ነው።

፩. የሰው ተፈጥሮው በእግዚአብሔር መልክ ነው (ዘፍ ፩፥ ፳፯፣ ፭፥፪) ይኸም ተፈጥሮ ነፍስ ያለው አሳቢና በሕይወት ያለ ነው። አንድ ነጠላ ሰው ሁኖ ሳለ መኖሩ [ነፍሱ] ከሕይወቱና ከምክንያቱ [አሳቢነቱ] የተለየ ነው። እንዲሁም ሦስቱ እርስ በእርስ የማይለያዩ ናቸው።

፪. “እኔ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ፥ በውስጥዋም ክብርን እሆናለሁ” (ዘካ ፪፥፭) በማለት ቤተ ክርስቲያኑን ሊጠብቃት ቃል ገብቶላታል። እንደ ሥላሴ አካላት በተመሳሳይ እሳት ሦስት መለያ ባህርያት አሉት፥ ነበልባል፣ ከነበልባሉ ወጥቶ የተወለደው ብርሃን እና ከነበልባሉ የተገኘው (የሰረጸው) ሙቀት። እዚህ ላይ ግን ማስተዋል የሚኖርብን አንዳቸውም ሌላኛቸውን ሁለቱን አይሞሉምና እነዚህ በራሳቸው አካላት አይደሉም። በብርሃን ውስጥ ብርሃንን እንረዳለን፥ በሙቀት ውስጥ ሙቀትን እንረዳለን።

፫. ፀሐይ የብርሃንና የሙቀት ጨረር የምትረጭ ፈለክ[16] ነች። ዳሩ ግን አንዲት (ነጠላ) ፀሐይ ብትሆንም። ፈለኳን ራሱዋን “ፀሐይ” ብለን እንጠራታለን፥ የብርሃኗን ጨረርም “ፀሐይ” ብለን እንጠራለን እንዲሁም በተመሳሳይ ሙቀቱን “ፀሐይ” ብለን እንጠራለን።

፬. እግዚአብሔር ከእንኮይ[17] ጋር የተያያዘ ነው። እንዲህ እንደተባለ “በዱር እንዳለ እንኮይ፥ እንዲሁ ውዴ በልጆች መካከል ነው።” (መኃልየ ፪፥፫) እንኮይ የምንበላው አካል፣ የምንቀምሰው ጣእም እና የምናሸተው መኣዛ አለው። እንኮይ በጣእሙ ወይም በመኣዛው ውስጥ ማወቅ (መለየት) እንችላለን።

_____________________

አባ ታድሮስ ማላቲ አዘጋጅተውቅ/ሚናስ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ያቀረበችውን ቤተ ፍቅር ዘአቢሲኒያ እንደተረጎመውጥር ፳፻፰ ዓ.ም

 

[1]It is the Oneness of substantial unity that is remote from isolation.

[2][መነሻ እና ማለቂያው የማይታወቅ (የሌለው) ጊዜ]

[3]Rationa existence- የሰው ልጅ ከእንሰሳ በማሰቡ እንደሚለየው ያለ

[4]Logos

[5]በዚህ አንቀጽ ላይ ባህርይ የሚለው essences የሚለው ቃል ትርጉም ነው።

[6]Being [አካል]

[7]essences

[8]የመለኮታዊ መኖርየራሱ አካል ነች።

[9]Being

[10]essences

[11]Being

[12]ዝኒ ከማሁ

[13]ዝኒ ከማሁ

[14]ነገረ ሃሳብ

[15]ምክንያት

[16]planet

[17]Apple

Leave a comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

Start a Blog at WordPress.com.

Up ↑